ፊልጵስዩስ 1:19-26

ፊልጵስዩስ 1:19-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ። በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል። እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ። ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም። በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም። ደግ​ሞም ስለ እና​ንተ በሕ​ይ​ወተ ሥጋ ብኖር ይሻ​ላል። ይህ​ንም ዐውቄ ለማ​ደ​ጋ​ች​ሁና በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ለም​ታ​ገ​ኙት ደስታ እን​ደ​ም​ኖር አም​ና​ለሁ። ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።

ፊልጵስዩስ 1:19-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሌላው የምደሰትበት ምክንያት በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ ስለማውቅ ነው። በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ። ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ጥቅም የሚገኝበት ነገር ነው። ይሁን እንጂ በዚሁ ሥጋዊ አካሌ ቀጥዬ የምኖር ብሆን ፍሬ የሚሰጥ ሥራ መሥራት ማለት ነው፤ ሆኖም ግን ቀጥዬ ከመኖርና ከመሞት የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም። በእነዚህ በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ተይዤአለሁ፤ በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለ ሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ ይኸውም ከክርስቶስ ጋር መኖር እጅግ የተሻለ ስለ ሆነ ነው። በሌላ በኩል በሕይወት መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው። በዚህ በመተማመን እኔ ከሞት ተርፌ እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ ዐውቃለሁ። እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ በእኔ ምክንያት ያላችሁ ትምክሕት በኢየሱስ ክርስቶስ ይበዛል።

ፊልጵስዩስ 1:19-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ እርዳታ አማካይነት ለመዳኔ እንደሚሆንልኝ አውቄያለሁና፤ ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ። ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በሥጋ መኖር ማለት ለእኔ ፍሬያማ ሥራ የምሠራበት ቢሆን፥ ምን እንደምመርጥ አላውቅም። በእነዚህም በሁለቱ አማራጮች መካከል እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን ስለ እናንተ በሥጋ መኖሬ ይበልጥ አስፈላጊ ነገር ነው። ይህንንም ተረድቼ፥ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ ከእናንተ ከሁላችሁም ጋር እንደምቈይና እንደምኖር አውቃለሁ፤ በዚህም በእናንተ ዘንድ እንደገና ስለ መገኘቴ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ መመካታችሁ በእኔ እንዲበዛላችሁ ነው።