ፊልጵስዩስ 1:1-8

ፊልጵስዩስ 1:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤ ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን። እና​ን​ተን በማ​ስ​ብ​በት ጊዜ ሁሉ ዘወ​ትር አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። ስለ እና​ን​ተም ሁል​ጊዜ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የደ​ስታ ጸሎ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ከእኔ ጋር አንድ በመ​ሆ​ና​ችሁ፥ እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ። ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና። በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።

ፊልጵስዩስ 1:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። እናንተን በማስታውስበት ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ ጸሎቴ በደስታ የተሞላ ነው። ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስከ አሁን ወንጌልን በመስበክ የሥራዬ ተባባሪዎች ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ሕይወት ውስጥ የጀመረ አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በሚመለስበት ቀን ወደ ፍጻሜ እንደሚያደርሰው እርግጠኛ ነኝ። አሁን በእስር ቤት ባለሁበት ጊዜና ከመታሰሬም በፊት ለወንጌል እውነት ለመከላከልና እርሱንም ለማጽናት እግዚአብሔር በጸጋው በሰጠኝ ዕድል ሁላችሁም ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ እናንተ ሁልጊዜ በልቤ ናችሁ። ስለዚህም ስለ እናንተ የሚሰማኝ ስሜት ትክክል ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያኽል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።