ዘኍልቍ 26:1-4
ዘኍልቍ 26:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንዲህም ሆነ፦ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና ካህኑን አልዓዛርን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብለው ነገሩአቸው፦ “እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግብፅ ምድር የወጡ የእስራኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው።
ዘኍልቍ 26:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
ዘኍልቍ 26:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም ሆነ፤ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮን ልጅ አልዓዛርን፦ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ ብሎ ተናገራቸው። ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ፦ እግዚአብሔር ሙሴን ከግብፅም ምድር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝቡን ቍጠሩ ብለው ተናገሩአቸው።
ዘኍልቍ 26:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
መቅሠፍቱ ከቆመ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ “በመላው የእስራኤል ማኅበር በየቤተሰቡ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውንና ከዚያም በላይ የሆኑትን፥ ወታደር ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ልጆች ሁሉ ቊጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው የሞአብ ሜዳ ሕዝቡን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦
ዘኍልቍ 26:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንዲህም ሆነ፤ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ ጌታ ሙሴንና የካህኑን የአሮን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፦ “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቁጠሩ።” ከግብጽም ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦