ዘኍልቍ 20:7-8
ዘኍልቍ 20:7-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።”
ያጋሩ
ዘኍልቍ 20 ያንብቡዘኍልቍ 20:7-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብስቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።”
ያጋሩ
ዘኍልቍ 20 ያንብቡዘኍልቍ 20:7-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 20 ያንብቡ