ዘኍልቍ 2:1-9

ዘኍልቍ 2:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ሥ​ር​ዐቱ፥ በየ​ዓ​ላ​ማው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ አን​ጻር ይስ​ፈሩ። በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም ሰባ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የሚ​ሰ​ፍሩ የይ​ሳ​ኮር ነገድ ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች አለቃ የሰ​ገር ልጅ ናት​ና​ኤል ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የዛ​ብ​ሎን ነገድ ነበረ፤ የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች አለቃ የኬ​ሎን ልጅ ኤል​ያብ ነበረ። የተ​ቈ​ጠሩ ሠራ​ዊ​ቱም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከይ​ሁዳ ሰፈር የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው መቶ ሰማ​ንያ ስድ​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ይጓ​ዛሉ።

ዘኍልቍ 2:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን አፋዛዥ ዙሪያ ይስፈሩ። በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳ ሰፈር ዓላማ ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮርም ልጆች አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የዛብሎን ነገድ ነበረ፤ የዛብሎንም ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።

ዘኍልቍ 2:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ እስራኤላውያን በየተመደቡበት ቡድን ሰንደቅ ዓላማና በየነገዳቸው ዐርማ ሥር ይሰፍራሉ፤ አሰፋፈራቸውም የመገናኛው ድንኳን በዙሪያው ሆኖ ፊታቸው ከድንኳኑ ትይዩ ይሆናል። ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው። የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። በእርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮር መሪም የጾዓር ልጅ ናትናኤል ነበር፤ የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ኀምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበር። ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎንም ልጆች መሪ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር። የእርሱም ክፍል ሰው ብዛት ኀምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበር። እንደየክፍላቸው በይሁዳ ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበር። በመጀመሪያ የሚጓዘው ይህ ቡድን ነበር።

ዘኍልቍ 2:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን ትይዩ በሁሉም አቅጣጫ ይስፈሩ። በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳን ሰፈር ዓላማ የያዙት ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮርም ልጆች አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ኀምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በእነርሱም አጠገብ የዛብሎን ነገድ ነበረ፤ የዛብሎንም ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበረ። ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ኀምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።