ዘኍልቍ 14:6-8 - Compare All Versions
ዘኍልቍ 14:6-8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ምድሪቱን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ “የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከመረጠን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል፤ እርስዋንም ይሰጠናል።
ዘኍልቍ 14:6-8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ምድሪቱን ከሰለሏት መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለመላው የእስራኤል ማኅበርም እንዲህ አሉ፤ “ዞረን ያየናትና የሰለልናት ምድር እጅግ ሲበዛ መልካም ናት። እግዚአብሔር በእኛ ደስ ከተሠኘብን ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደዚያች ምድር መርቶ ያገባናል፤ ለእኛም ይሰጠናል።
ዘኍልቍ 14:6-8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል።
ዘኍልቍ 14:6-8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ምድሪቱን እንዲያጠኑ ከተላኩት ሰዎች ሁለቱ የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፉኔ ልጅ ካሌብ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “መርምረን ያጠናናት ምድር እጅግ ውብ የሆነች ምድር ናት፤ እግዚአብሔር በእኛ ደስ የሚለው ቢሆን ወደዚያ ይወስደናል፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ያቺን ለም ምድር ይሰጠናል፤
ዘኍልቍ 14:6-8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም የሆነች ናት። ጌታስ በእኛ ደስ የሚሰኝ ቢሆን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርሷንም ይሰጠናል።