ዘኍልቍ 14:1-4 - Compare All Versions

ዘኍልቍ 14:1-4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጦ​ር​ነት እን​ሞት ዘንድ ወደ​ዚች ምድር ለምን ያገ​ባ​ናል? ሴቶ​ቻ​ች​ንና ልጆ​ቻ​ችን ለን​ጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ፤ አሁ​ንም ወደ ግብፅ መመ​ለስ አይ​ሻ​ለ​ን​ምን?” አሉ​አ​ቸው። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እን​መ​ለስ” ተባ​ባሉ።

ዘኍልቍ 14:1-4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚያች ሌሊት ማኅበረ ሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸና አለቀሰ። እስራኤላውያን በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሏቸው፤ “ምነው በግብጽ ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን ባረፍነው ኖሮ! እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር የሚያመጣን ለምንድን ነው? በሰይፍ እንድንወድቅ ነውን? ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ታዲያ ወደ ግብጽ መመለሱ አይሻለንም?” እርስ በርሳቸውም፣ “አለቃ መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ።

ዘኍልቍ 14:1-4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው ጮኹ፤ ሕዝቡም በዚያ ሌሊት አለቀሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ፦ በግብፅ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ! እግዚአብሔርም በሰይፍ እንሞት ዘንድ ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሴቶቻችንና ልጆቻችን ምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብፅ መመለስ አይሻለንምን? አሉአቸው። እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ።

ዘኍልቍ 14:1-4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሕዝቡም ሌሊቱን ሁሉ በመጨነቅ ሲጮኹ አደሩ፤ በሙሴና በአሮንም ላይ እንዲህ እያሉ አጒረመረሙ፥ “በግብጽ ሳለን ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን በቀረን መልካም በሆነ ነበር! እግዚአብሔር ወደዚያች ምድር የሚወስደን ለምንድን ነው? እኛ ሁላችን በጦርነት እናልቃለን፤ ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ወደ ግብጽ ብንመለስ መልካም አይሆንምን?” ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ኑ! መሪ የሚሆነን ሰው መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ!” ተባባሉ።

ዘኍልቍ 14:1-4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ፤ በዚያም ሌሊት ሕዝቡ አለቀሰ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በግብጽ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ! ጌታም በሰይፍ እንድንሞት ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ለምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?” እርስ በርሳቸውም፦ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ።