ነህምያ 7:1-3
ነህምያ 7:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹን አቆምሁ፤ በረኞቹንና መዘምራኑን፥ ሌዋውያኑንም ሾምሁ፤ ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። እኔም፥ “ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፤ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው፥ አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቂዎችን አስቀምጡ” አልኋቸው።
ነህምያ 7:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ። በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው። ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያድርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።
ነህምያ 7:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥ ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፥ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። እኔም፦ ፀሀይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፥ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፥ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው።
ነህምያ 7:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር። እኔም የኢየሩሳሌምን ከተማ ያስተዳድሩ ዘንድ ሁለት ሰዎችን ሾምኩ፤ እነርሱም የእኔ ወንድም የሆነው ሐናኒና የምሽግ ኀላፊ የነበረው ሐናንያ ናቸው፤ ሐናንያ እውነተኛና እግዚአብሔርን በመፍራት ረገድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰው ነበር። ለእነርሱም የሰጠኋቸው መመሪያ የኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ እንዳይከፈቱ፥ ደግሞ ማታ ፀሐይ ስትጠልቅ የዘብ ጠባቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት የቅጽር በሮቹ በቊልፍና በመወርወሪያ አጥብቀው እንዲዘጉአቸው ነበር። እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል ሰዎችን ቀጥረው ከፊሎቹ በሥራቸው ላይ ሆነው ሌሎቹ ደግሞ በየቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው እንዲጠብቁ አዘዝኳቸው።
ነህምያ 7:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንዲህም ሆነ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ በሮቹን ካቆምሁ በኋላ፥ በር ጠባቂዎች፥ መዘምራንና ሌዋውያን ተሾሙ፤ ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። እኔም እንዲህ አልኋቸው፦ የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስኪል ድረስ አይከፈቱ፥ በሚቆሙበት ጊዜ በሮቹን ይዝጉ፥ ይቆልፉትም፤ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዱን በተራው አንዳንዱን ደግሞ በየቤቱ አጠገብ ጠባቂዎች ይሾሙ።