ነህምያ 4:12-14
ነህምያ 4:12-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአጠገባቸውም የተቀመጡት አይሁድ መጥተው፥ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን።” ከቅጥሩም በስተኋላ በኩል ባለው በታችኛው ክፍል በሰዋራ ስፍራ ሰይፋቸውንና ጦራቸውን፥ ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው፤ አይችም ተነሣሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን አምላካችንን አስቡ፤ ስለ ወንድሞቻችሁም፥ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ስለ ሚስቶቻችሁም፥ ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ” አልኋቸው።
ነህምያ 4:12-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም በአጠገባቸው የሚኖሩ አይሁድ መጥተው፣ “እናንተ የትም ቦታ ብትሆኑ፣ እኛን ማጥቃታቸው አይቀርም!” በማለት ዐሥር ጊዜ ደጋግመው ነገሩን። ስለዚህ ከቅጥሩ በስተኋላ በሚገኙ ግልጽ ቦታዎች ላይ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ሰይፋቸውን፣ ጦራቸውንና ቀስታቸውን እንደ ያዙ በየቤተ ሰባቸው በመመደብ ቦታቸውን እንዲይዙ አደረግሁ። ነገሩን በጥሞና ከተመለከትሁ በኋላ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና የቀረውን ሕዝብ፣ “አትፍሯቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፤ ስለ ወንድሞቻችሁ፣ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ስለ ሚስቶቻችሁና ስለ ቤት ንብረታችሁ ተዋጉ” አልኋቸው።
ነህምያ 4:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በአጠገባቸውም የተቀመጡት አይሁድ መጥተው፦ ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል ብለው አሥር ጊዜ ነገሩን። ከቅጥሩም በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን ጦራቸውንም ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው። አይቼም ተነሣሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው፥ ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ አልኋቸው።
ነህምያ 4:12-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በጠላቶቻችን መካከል የሚኖሩ አይሁድ ወደ ከተማው እየመጡ ጠላቶቻችን እኛን ለማጥቃት ያቀዱ መሆናቸውን ደጋግመው በማስጠንቀቅ ነገሩን። ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ። ሕዝቡ ተጨንቀው ስላየሁ፥ እነርሱንና መሪዎቻቸውን፥ ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ሁሉ “ከጠላቶቻችን የተነሣ አትፍሩ፤ ምን ያኽል ታላቅና ግርማው የሚያስፈራ አምላክ እንዳለንና እርሱ ስለ ወገኖቻችሁ፥ ስለ ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ስለ ቤት ንብረታችሁም እንደሚዋጋላችሁ አስታውሱ” አልኳቸው።