ነህምያ 12:1-47

ነህምያ 12:1-47 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ከዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና ከኢ​ያሱ ጋር የወ​ጡት ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን እነ​ዚህ ነበሩ፤ ሠራ​ህያ፥ ኤር​ም​ያስ፥ ዔዝራ፤ አማ​ርያ፥ መሎክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬ​ንያ፥ ሬሁም፥ ሜራ​ሞት፤ አዶ፥ ጌን​ቶን፥ አብያ፤ ሚያ​ሚን፥ መዓ​ድያ፥ ቤልጋ፤ ሰማ​ዕያ፥ ዮያ​ሪብ፥ ዮዳ​ኤያ፤ ሳሎም፥ ዓሞቅ፥ ሔል​ቅ​ያስ፥ ኢዳ​ዕያ፤ እነ​ዚህ በኢ​ያሱ ዘመን የካ​ህ​ና​ቱና የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ። ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያሱ፥ በንዊ፥ ቀድ​ም​ኤል፥ ሰራ​ብያ፥ ይሁዳ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በመ​ዘ​ም​ራን ላይ የተ​ሾመ ማታ​ንያ። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በቅ​ቡ​ቅ​ያና ዑኒ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ነበሩ። ኢያ​ሱም ዮአ​ቂ​ምን ወለደ፤ ዮአ​ቂ​ምም ኤሊ​ያ​ሴ​ብን ወለደ፤ ኤሊ​ያ​ሴ​ብም ዮሐ​ዳን ወለደ፤ ዮሐ​ዳም ዮና​ታ​ንን ወለደ፤ ዮና​ታ​ንም ይዱ​ዕን ወለደ። በዮ​አ​ቂ​ምም ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናቱ ነበሩ፤ ከሠ​ራያ ምራያ፥ ከኤ​ር​ም​ያስ ሐና​ንያ፤ ከዕ​ዝራ ሜሱ​ላም፥ ከአ​ማ​ርያ ዮሐ​ናን፤ ከማ​ሎክ ዮና​ታን፥ ከሴ​ብ​ንያ ዮሴፍ፤ ከሐ​ሪም ዓድና፥ ከመ​ራ​ዮት ሔል​ቃይ፤ ከአዶ ዘካ​ር​ያስ፥ ከጌ​ን​ቶን ሜሱ​ላም፤ ከአ​ብያ ዝክሪ፥ ከሚ​ያ​ሚ​ንና ከሞ​ዓ​ድያ፥ ፈል​ጣይ፤ ከቤ​ልጋ ሳሙኣ፥ ከሰ​ማ​ዕያ ዮና​ታን፤ ከዮ​ያ​ሬብ መት​ናይ፥ ከዮ​ዳ​ኤያ ኦዚ፤ ከሳ​ላይ ቃላይ፥ ከዓ​ሞቅ ዔቤር፤ ከኬ​ል​ቅ​ያስ ሐሳ​ብያ፥ ከኢ​ዳ​ዕያ ናት​ና​ኤል። ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በኤ​ል​ያ​ሴ​ብና በዮ​ሐዳ፥ በዮ​ሐ​ና​ንና በያ​ዱዕ ዘመን የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ተጻፉ፤ ካህ​ና​ቱም በፋ​ር​ሳ​ዊው በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥት ዘመን ተጻፉ። የሌዊ ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እስከ ኤል​ያ​ሴብ ልጅ እስከ ዮሐ​ናን ዘመን ድረስ በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጻፉ። የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። መታ​ንያ፥ በቅ​ቡ​ቅያ፥ አብ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ጤል​ሞን፥ ዓቁብ በበ​ሮች አጠ​ገብ የሚ​ገ​ኙ​ትን ዕቃ ቤቶች ለመ​ጠ​በቅ በረ​ኞች ነበሩ። እነ​ዚ​ህም በኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ በኢ​ያሱ ልጅ በዮ​አ​ቂም በአ​ለ​ቃ​ውም በነ​ህ​ምያ፥ በጸ​ሓ​ፊ​ውም በካ​ህኑ በዕ​ዝራ ዘመን ነበሩ። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር በተ​መ​ረቀ ጊዜ ምረ​ቃ​ውን በደ​ስ​ታና በም​ስ​ጋና፥ በመ​ዝ​ሙ​ርም፥ በጸ​ና​ጽ​ልም፥ በበ​ገ​ናም፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ለማ​ድ​ረግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ኑን በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ሁሉ ፈለጉ። የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም ልጆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙር​ያና ከሌ​ሎ​ችም መን​ደ​ሮች ተሰ​በ​ሰቡ። ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና። ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ። የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ወደ ቅጥሩ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ አመ​ስ​ጋ​ኞ​ቹ​ንም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ተርታ አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ የአ​ን​ዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅ​ጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣ​ያው በር ሄዱ። ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ሆሴዕ የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች እኩ​ሌታ፤ ዓዛ​ርያ፥ ዕዝራ፥ ሜሱ​ላም፥ ይሁዳ፥ ብን​ያም፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤር​ም​ያስ፤ መለ​ከ​ትም ይዘው ከካ​ህ​ናቱ ልጆች አያ​ሌ​ዎች፥ የአ​ሳ​ፍም ልጅ የዘ​ኩር ልጅ የሚ​ካያ ልጅ የመ​ታ​ንያ ልጅ የሰ​ማ​ዕያ ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ዘካ​ር​ያስ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕያ፥ አዘ​ር​ኤል፥ ማዕ​ላይ፥ ጌላ​ላይ፥ መዓይ፥ ናት​ና​ኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው የዳ​ዊ​ትን የዜ​ማ​ውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ በፊ​ታ​ቸው ነበረ። በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም የአ​መ​ስ​ጋ​ኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ነበ​ርን፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ፥ በእ​ቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ። እን​ዲሁ ሁለቱ የአ​መ​ስ​ጋ​ኞች ክፍ​ሎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቆሙ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እኔና የአ​ለ​ቆች እኩ​ሌታ ነበ​ርን፤ ካህ​ና​ቱም ኤል​ያ​ቄም፥ መዕ​ሤያ፥ ሚን​ያ​ሚን፥ ሚካያ፥ ኤል​ዮ​ዔ​ናይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሐና​ንያ መለ​ከት ይዘው፥ መዕ​ሤያ፥ ሰማ​ዕያ፥ ኤል​የ​ዜር፥ ኦዚ፥ ዮሐ​ናን፥ ሚል​ክያ፥ ኤላም፥ ኤዝር፥ መዘ​ም​ራ​ኑም በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ይዝ​ረ​አያ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ደስታ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ደስም አላ​ቸው፤ ሴቶ​ቹና ልጆ​ቹም ደግሞ ደስ አላ​ቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሩቅ ተሰማ። የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ። እነ​ር​ሱም መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ሥር​ዐት የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውን ሥር​ዐት እንደ ዳዊ​ትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎ​ሞን ትእ​ዛዝ ጠበቁ። በዳ​ዊ​ትም ዘመን አሳፍ የመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ነበር፤ እነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዜማ ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና በነ​ህ​ምያ ዘመን ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑና ለበ​ረ​ኞቹ ፈን​ታ​ቸ​ውን በየ​ዕ​ለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ነገር ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር ለአ​ሮን ልጆች ሰጡ።

ነህምያ 12:1-47 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋራ የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣ አማርያ፣ መሉክ፣ ሐጡስ፣ ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣ አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣ ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣ ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣ ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ። እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋራ የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ። ወንድሞቻቸው የሆኑት በቅቡቅያና ዑኒም በአገልግሎት ጊዜ ከእነርሱ ትይዩ ይቆሙ ነበር። ኢያሱ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂም ኤልያሴብን ወለደ፤ ኤልያሴብ ዮአዳን ወለደ፤ ዮአዳ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ። በዮአቂም ዘመን የካህናቱ ቤተ ሰብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ከሠራያ ቤተ ሰብ፣ ምራያ፤ ከኤርምያስ፣ ሐናንያ፤ ከዕዝራ፣ ሜሱላም፤ ከአማርያ፣ ዮሐናን፤ ከሙሊኪ፣ ዮናታን፤ ከሰበንያ፣ ዮሴፍ፤ ከካሪም፣ ዓድና፤ ከመራዮት፣ ሔልቃይ፤ ከአዶ፣ ዘካርያስ፤ ከጌንቶን፣ ሜሱላም፤ ከአብያ፣ ዝክሪ፤ ከሚያሚንና ከሞዓድያ፣ ፈልጣይ፤ ከቢልጋ፣ ሳሙስ፤ ከሸማያ፣ ዮናታን፤ ከዮያሪብ፣ መትናይ፤ ከዮዳኤ፣ ኦዚ፤ ከሰሉ፣ ቃላይ፤ ከዓሞቅ፣ ዔቤር፤ ከኬልቅያስ፣ ሐሸብያ፤ ከዮዳኤ፣ ናትናኤል። በኤልያሴብ፣ በዮአዳ፣ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆችና ካህናቱ፣ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር። በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ። እነዚህም በኢዮሴዴቅ ልጅ፣ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም፣ በአገረ ገዥ በነህምያ፣ በካህኑና በጸሓፊው በዕዝራ ዘመን አገለገሉ። የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። መዘምራኑንም እንደዚሁ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለው ከነጦፋውያን መንደሮች በአንድነት ሰበሰቧቸው። በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤትጌልገላ፣ ከጌባዕና ከዓዝሞት አካባቢ ነው። ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ። እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ። እነዚህንም ሆሻያና ከይሁዳ አለቆች እኩሌቶቹ ተከተሏቸው፤ የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣ ከይሁዳ፣ ከብንያም፣ ከሸማያ፣ ከኤርምያስና፣ እንዲሁም መለከት ከያዙ ጥቂት ካህናትና ከአሳፍ ልጅ፣ ከዛኩር ልጅ፣ ከሚካያ ልጅ ከመታንያ ልጅ፣ ከሸማያ ልጅ፣ ከዮናታን ልጅ፣ ከዘካርያስ ጋራ ነበር። ወንድሞቹ ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳና አናኒም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የዜማ መሣሪያዎቹን ይዘው ሄዱ፤ ሰልፉን የሚመራውም ጸሓፊው ዕዝራ ነበረ። ከምንጭ በር ተነሥተው በቀጥታ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎች ወጡ፤ ከዚያም በቅጥሩ መውጫ በኩል አድርገው ከዳዊት ቤት በላይ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ በር ሄዱ። ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለተኛው ቡድን በስተግራ በኩል ሄደ፤ እኔም ከከፊሉ ሕዝብ ጋራ ሆኜ በቅጥሩ ግንብ ላይ፣ የእቶኑን ግንብ በማለፍ እስከ ሰፊው ቅጥር ተከተልኋቸው፤ ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ በጎች በር ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም በዘበኞች በር አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ። ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋራ ቦታዬን ያዝሁ፤ እንደዚሁም ካህናቱ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሐናንያ መለከታቸውን ይዘው፣ መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ዮሐናን፣ መልክያ፣ ኤላምና ኤጽር ቦታቸውን ያዙ፤ መዘምራኑ በይዝረሕያ መሪነት ዘመሩ። እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር። በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና። እንደ መዘምራኑና በር ጠባቂዎቹ ሁሉ፣ እነዚህም የአምላካቸውን አገልግሎትና የመንጻቱን ሥርዐት በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ፈጸሙ። ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር።

ነህምያ 12:1-47 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፥ ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥ መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥ አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን፥ መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሻማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ፥ ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፥ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። ሌዋውያኑም፥ ኢያሱ፥ ቢንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የነበረ መታንያ። ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ። ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥ ዮአዳም ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታንም ያዱአን ወለደ። በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ካህናቱ ነበሩ፥ ከሠራያ ምራያ፥ ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥ ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከመሉኪ ዮናታን፥ ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥ ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፥ ከአብያ ዝክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥ ፈልጣያ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን፥ ከዮያሪብ መትናይ፥ ከዮዳኤ ኦዚ፥ ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥ ከኬልቅያስ ሐሸብያ፥ ከዮዳኤ ናትናኤል። ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፥ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ። የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ። የሌዋውያኑም አለቆች ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር። መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ። እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ። የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ። መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፥ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ። የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ። ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኩሌታ፥ ዓዛርያስ፥ ዕዝራ፥ ሜሱላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማያ፥ ኤርምያስ፥ መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሸማያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥ ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፥ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ። በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፥ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፥ እኔና የሕዝቡም እኩሌታ በስተኋላቸው ነበርን፥ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፥ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኩሌታ፥ ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ መልክያ፥ ኤላም፥ ኤጽር ቆምን። መዘምራኑም በትላቅ ድምፅ ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ። እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፥ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፥ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ። ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኩራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ። አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።

ነህምያ 12:1-47 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከሊቀ ካህናቱ ከኢያሱ ጋር ከምርኮ የተመለሱት የካህናትና የሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፤ ካህናት፦ ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥ ማሉክ፥ ሐጡሽ፥ ሸካንያ፥ ረሑም፥ መሬሞት፥ ዒዶ፥ ጊነቶን፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥ መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማዕያ፥ ዮያሪብ፥ ይዳዕያ፥ ሳሉ፥ ዓሞክ፥ ሒልቂያና ይዳዕያ። እነዚህ ሰዎች በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ ዘመን የወገኖቻቸው ካህናት መሪዎች የነበሩ ናቸው። ሌዋውያን፦ የምስጋና መዝሙር ኀላፊዎች የነበሩት ሌዋውያን ኢያሱ፥ ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሼሬብያ፥ ይሁዳና ማታንያ ነበሩ። ባቅቡቅያ፥ ዑኖና ሌሎችም ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ከእነርሱ ጋር በመቀባበል ይዘምሩ ነበር። ኢያሱ ዮያቂምን ወለደ፤ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፤ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፤ ዮያዳዕ ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታን ያዱዓን ወለደ። ዮያቂም ሊቀ ካህናት በነበረበት ዘመን ከዚህ የሚከተሉት ካህናት፥ የካህናት ጐሣዎች አለቆች ነበሩ፦ ካህኑ ጐሣው። መራያ ሠራያ። ሐናንያ ኤርምያስ። መሹላም ዕዝራ። የሆሐናን አማርያ። ዮናታን መሉኪ። ዮሴፍ ሸካንያ። ዓድና ሓሪም። ሔልቃይ መራዮት። ዘካርያስ ዒዶ። መሹላም ጊነቶን። ዚክሪ አቢያ። ሚንያሚን ፒልጣይ ሞዓዲያ። ሻሙዐ ቢልጋ። የሆናታን ሸማዕያ። ማትናይ ዮያሪብ። ዑዚ ይዳዕያ። ቃላይ ሳላይ። ዔቤር ዓሞቅ። ሐሻብያ ሒልቂያ። ናትናኤል ይዳዕያ። ኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮናታንና ያዱዐ ተብለው የሚጠሩት ሊቃነ ካህናት በኖሩበት ዘመን የሌዋውያንና የካህናት ቤተሰብ አለቆች ተለይተው የሚታወቁበት መዝገብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ይህም መዝገብ የተዘጋጀው ዳርዮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ የሌዋውያን ቤተሰብ አለቆች በግልጽ መዝገብ የታወቁት የኤልያሺብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮናታን በሕይወት እስከ ኖረበት ዘመን ብቻ ነበር። ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። በቤተ መቅደሱ ቅጽር በር አጠገብ የተሠሩትን የዕቃ ግምጃ ቤቶች የሚጠብቁ ዘበኞችም ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ መሹላም፥ ጣልሞንና ዓቁብ ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። እነዚህም የኢዮጼዴቅ የልጅ ልጅ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዮያቂም፥ አገረ ገዢው ነህምያ ካህኑና የሕግ ሊቁ ዕዝራ በነበሩበት ዘመን የተመደቡ አገልጋዮች ነበሩ። የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር የምረቃ በዓል በተከበረበት ዕለት ሌዋውያኑ በጸናጽል፥ በበገናና በመሰንቆ በዓሉን እንዲያከብሩ ከየሚኖሩበት ስፍራ ተፈልገው መጡ። ይህንንም በዓል ለማክበር የሌዋውያኑ ቤተሰቦች መዘምራን ሁሉ ሰፍረው ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም አካባቢና በነጦፋ ከሚገኙት ታናናሽ ከተሞች፥ ከቤትጊልጋል፥ ከጌባዕና ከዓዝማዌት ተሰብስበው መጡ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ስለ ሕዝቡ ራሳቸው ስለ ከተማይቱ በሮችና ስለ ቅጽሩ የማንጻትን ሥርየት ፈጸሙ። እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤ ሆሻዕያና የይሁዳ መሪዎች ተከተሉአቸው። ዐዛርያ፥ ዕዝራ፥ መሹላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማዕያና ኤርምያስ ተብለው የሚጠሩት ካህናትም በሰልፍ አለፉ፤ ቀጥሎም እምቢልታ የሚነፉ ጥቂት ካህናትና እንዲሁም ዘካርያስ የዮናታን ልጅ የሸማዕያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚክያን ልጅ፥ የዛኩር ልጅ የአሳፍ ልጅ አለፉ። የራሱ ጐሣ አባላት የነበሩት ሸማዕያ፥ ዐዛርኤል፥ ሚለላይ፥ ጊለላይ፥ ማዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይዘምርበት የነበረውን የሙዚቃ መሣሪያ ሁሉ ተሸክመው ተከተሉት፤ የዚህንም ቡድን ሰልፍ የሚመራው የሕግ ሊቁ ዕዝራ ነበር። ወደ ውሃው ምንጭ በር እንደ ደረሱም ወደ ዳዊት ከተማ አቅንተው በቅጽሩ ላይ ያሉትን ደረጃዎች በመውጣትና የዳዊትን ቤተ መንግሥት በማለፍ ከከተማይቱ በስተምሥራቅ ወደሚገኘው ወደ ውሃ ቅጽር በር ተመለሱ። ሌላው የመዘምራን ቡድን ሰልፍ የቅጽሩን ግንብ ጫፍ በመከተል ወደ ግራ በኩል አለፈ፤ እኔም ከሕዝቡ እኩሌታ ጋር ይህንኑ የቡድን ሰልፍ እከተል ነበር፤ የእቶኑንም ግንብ አልፈን ወደ ሰፊው ቅጽር ግንብ ደረስን። ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር። በዚህም ሁኔታ የሁለቱም ቡድኖች ሰልፍ እግዚአብሔርን በመዝሙር በማመስገን ወደ ቤተ መቅደሱ ክልል ደረሰ፤ አብረውኝም ከነበሩት መሪዎች ጋር በተጨማሪ፥ የእኔ ቡድን ሰልፍ ከዚህ የሚከተሉትን እምቢልታ የሚነፉ ካህናትን የሚጨምር ነበር፤ እነርሱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ማካያ፥ ኤልዮዔናይ፥ ዘካርያስና ሐናንያ ሲሆኑ፥ እነርሱንም ደግሞ መዕሤያ፥ ሸማዕያ፥ አልዓዛር፥ ዑዚ፥ የሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ኤላምና ኤዜር ተከትለዋቸው ይጓዙ ነበር፤ እንደ ቆምንም መዘምራኑ በይዝራሕያ እየተመሩ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ዘመሩ። በዚያም ዕለት ብዙ መሥዋዕት ቀረበ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔር ደስ ስላሰኛቸው ታላቅ ሐሴት አደረጉ፤ ሴቶችም፥ ልጆችም አብረው ተደስተዋል፤ በኢየሩሳሌም የነበረው የእልልታቸው ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር። በዚያም ጊዜ ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚደረገውን አስተዋጽዖ እንዲሁም ከዐሥር አንዱን፥ በየዓመቱ በመጀመሪያ የሚደርሰውን እህልና ፍራፍሬ በማከማቸት የዕቃ ቤት ክፍሎችን የሚጠብቁ ኀላፊዎች ተሾሙ፤ እነዚህም ሰዎች በልዩ ልዩ ከተሞች አቅራቢያ ከሚገኙ የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የተመደበውን አስተዋጽዖ የመሰብሰብ ኀላፊነት ነበራቸው፤ የይሁዳም ሕዝብ በሙሉ በካህናቱና በሌዋውያኑ እጅግ ደስ ብሎአቸው ነበር። የይሁዳም ሕዝብ ተደስቶ የነበረው እነርሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መፈጸም የሚገባውን ደንብና የማንጻት ሥርዓት በማከናወናቸው ነበር፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራንና የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎችም ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን በመደቡት ሥርዓት መሠረት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ፈጸሙ። ከንጉሥ ዳዊትና የመዘምራን አለቃ ከነበረው አሳፍ ዘመንም ጀምሮ ለመዘምራንና ለማኅሌታዊ ዜማ መሪዎች ነበሩአቸው። በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን መላው እስራኤላውያን ለቤተ መቅደሱ መዘምራንና ለዘብ ጠባቂዎቹ የየዕለት ድርሻቸውን ይሰጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም የአሮን ተወላጁን ድርሻ ይሰጡ ነበር።

ነህምያ 12:1-47 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ናቸው፤ ሥራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥ ማሉክ፥ ሐጡሽ፥ ሽካንያ፥ ርሁም፥ ምሬሞት፥ ዒዶ፥ ጊንቶይ፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥ ማዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሽማዕያ፥ ዮያሪብ፥ ይዳዕያ፥ ሳሉ፥ ዓሞቅ፥ ሒልቂያ፥ ይዳዕያ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ። ሌዋውያኑም፦ ኢያሱ፥ ቢኒዊ፥ ቃድሚኤል፥ ሼሬብያ፥ ይሁዳና ከወንድሞቹ ጋር በመሆን የምስጋና መዝሙር ኃላፊ የነበረው ማታንያ። ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያና ዑኖ በአገልግሎቱ ጊዜ በፊት ለፊታቸው ይቆሙ ነበር። ኢያሱም ዮያቂምን ወለደ፥ ዮያቂም ኤልያሺብን ወለደ፥ ኤልያሺብ ዮያዳዕን ወለደ፥ ዮያዳዕ ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታን ያዱዓን ወለደ። በዮያቂም ዘመን የአባቶች መሪዎች ካህናቱ እነዚህ ነበሩ፦ ከሥራያ ቤተሰብ ምራያ፥ ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ምሹላም፥ ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከምሉኪ ዮናታን፥ ከሽባንያ ዮሴፍ፥ ከሐሪም ዓድና፥ ከምራዮት ሔልቃይ፥ ከዒዶ ዘካርያስ፥ ከጊንቶን ምሹላም፥ ከአቢያ ዚክሪ፥ ከሚንያሚን፥ ከሞዓድያ፥ ፒልጣይ፥ ከቢልጋ ሻሙዓ፥ ከሽማዕያ ይሆናታን፥ ከዮያሪብ ማትናይ፥ ከይዳዕያ ዑዚ፥ ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥ ከሒልቂያ ሐሻብያ፥ ከይዳዕያ ናትናኤል። ከሌዋውያኑም በኤልያሺብ፥ ዮያዳዕ፥ ዮሐናን፥ ያዱዓ ዘመን የአባቶች መሪዎችና ካህናቱ በፋርሳዊው በዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ተመዝግበው ነበር። የሌዊ ልጆች የአባቶች መሪዎች እስከ ኤልያሺብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር። ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ምሹላም፥ ጣልሞን፥ ዓቁብ በበሮቹ አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ። እነዚህ በዮፃዳቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮያቂም ዘመንና በገዢው በነህምያና በጸሐፊው በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ። የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ። የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ተሰበሰቡ፤ መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፥ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ። የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ። ከእነርሱም በኋላ ሆሻዕያና የይሁዳ መሪዎች እኩሌታ ሄዱ፥ አዛርያ፥ ዕዝራ፥ ምሹላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማዕያና ኤርምያስ፥ መለከት የያዙ ጥቂት የካህናቱ ልጆች፥ የአሳፍ ልጅ፥ የዛኩር ልጅ፥ የሚካያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሸማዕያ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥ ወንድሞቹም ሸማዕያ፥ ዓዛርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው የዳዊትን የዜማ መሣሪያ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊው ዕዝራም በፊታቸው ነበረ። “በምንጭ በር” አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። ከፊት ይሄድ የነበረው ሁለተኛው የምስጋና መዘምራን ክፍል ነበር፤ እኔና የሕዝቡ እኩሌታ በስተ ኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ ከ “የእቶኑ ግንብ” በላይ እስከ “ሰፊው ቅጥር” ድረስ፥ ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። ሁለቱ የምስጋና መዘምራን ክፍሎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፥ እኔና ከመሪዎቹ እኩሌታ በተጨማሪ፥ ካህናቱ ኤልያቂም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዕናዪ፥ ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሽማዕያ፥ አልዓዛር፥ ኡዚ፥ ይሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ዔላም፥ ዓዜር ቆምን። መዘምራኑም በዪዝራሕያ መሪነት በታላቅ ድምፅ ዘመሩ። እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ። በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ። አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።