ናሆም 1:3-7
ናሆም 1:3-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፣ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው። ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። ተራሮችም ከእርሱ የተነሣ ታወኩ፥ ኮረብቶችም ቀለጡ፣ ምድርና ዓለም የሚኖሩበትም ሁሉ ከፊቱ ተናወጡ። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ። እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።
ናሆም 1:3-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ በኀይሉም ታላቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደለኛውን ሳይቀጣ አያልፍም፤ መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በማዕበል ውስጥ ነው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው። ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል። ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስም አበቦች ረግፈዋል። ተራሮች በፊቱ ታወኩ፤ ኰረብቶችም ቀለጡ። ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩት ሁሉ ተናወጡ። ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል። እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤
ናሆም 1:3-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ታጋሽና ኀያል ነው፤ ነገር ግን በደለኛውን ሳይቀጣው አያልፍም፤ መንገዱ በዐውሎ ነፋስና በሞገድ ውስጥ ነው፤ ሰው ሲራመድ ትቢያን እንደሚያስነሣ፥ የእግዚአብሔርም መገለጥ ደመናን ያስከትላል። እግዚአብሔር ባሕሩንና ወንዞቹን ገሥጾ ያደርቃቸዋል። በባሳንና በቀርሜሎስ የሚገኙ ዕፀዋት ይደርቃሉ፤ የሊባኖስም አበቦች ይጠወልጋሉ። በእግዚአብሔር ፊት ተራራዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ኰረብቶችም ይቀልጣሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ትናወጣለች፤ ዓለምና በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ። በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ። እግዚአብሔር ቸር ነው፤ በመከራ ጊዜም ጠንካራ መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ ይንከባከባል።
ናሆም 1:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው። ባሕሩንም ይገሥጻል፥ ያደርቀዋልም፥ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፤ ባሳንና ቀርሜሎስም ጠውልጎአል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። ተራሮችም ከእርሱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ቀለጡ፤ ምድር፥ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ በፊቱ ተረበሹ። በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ። ጌታ መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚሸሸጉትን ያውቃል።