ማርቆስ 2:3-5 - Compare All Versions
ማርቆስ 2:3-5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሰዎችም አንድ ሽባ በአራት ሰዎች አሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ እርሱ ወዳለበት ሊያቀርቡት ስላልቻሉ፣ የቤቱን ጣራ እርሱ ባለበት በኩል ነድለው ቀዳዳ በማበጀት ሽባው የተኛበትን ዐልጋ በዚያ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ማርቆስ 2:3-5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በዚያን ጊዜ አራት ሰዎች አንድ ሽባ ሰው ተሸክመው ወደ እርሱ መጡ። ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ኢየሱስ ማቅረብ ቢያቅታቸው የቤቱን ጣራ ኢየሱስ ባለበት በኩል ከፍተው ሽባውን ከነአልጋው አወረዱት። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “ልጄ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።
ማርቆስ 2:3-5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት። ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
ማርቆስ 2:3-5 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት። ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፥ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
ማርቆስ 2:3-5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
አራት ሰዎችም አንድ ሽባ ሰው ተሸክመው አመጡለት። ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ ማቅረብ ስላልቻሉ፥ እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤” አለው።