ማቴዎስ 9:21-22 - Compare All Versions

ማቴዎስ 9:21-22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በልብዋ “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ትል ነበረችና። ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ! አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤” አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።

ማቴዎስ 9:21-22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርሷም በልቧ፣ “የልብሱን ጫፍ እንኳ ብነካ እፈወሳለሁ” ብላ ነበር። ኢየሱስም ወደ ኋላ ዘወር ብሎ ሴቲቱን አያትና፣ “አይዞሽ፣ ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ተፈወሰች።

ማቴዎስ 9:21-22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በልብዋ፦ ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና። ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና፦ ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።

ማቴዎስ 9:21-22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይህንንም ያደረገችው “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ በልብዋ አስባ ስለ ነበር ነው። ኢየሱስም መለስ ብሎ አያትና “አይዞሽ ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴትዮዋም ወዲያውኑ ዳነች።

ማቴዎስ 9:21-22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በልብዋ “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ፤” ብላ ታስብ ነበርና። ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ! አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል፤” አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።