ማቴዎስ 8:1-3
ማቴዎስ 8:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ “ጌታ ሆይ! ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 ያንብቡማቴዎስ 8:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከተራራው በወረደ ጊዜም ብዙ ሕዝብ ተከተለው። እነሆ፤ አንድ ለምጻም ሰው ወደ ኢየሱስ ቀረበና ከፊቱ ተንበርክኮ እየሰገደለት፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው። ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 ያንብቡማቴዎስ 8:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 ያንብቡ