ማቴዎስ 7:9-11
ማቴዎስ 7:9-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወይስ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!
ያጋሩ
ማቴዎስ 7 ያንብቡማቴዎስ 7:9-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጥ አለን? ወይም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጥ?
ያጋሩ
ማቴዎስ 7 ያንብቡማቴዎስ 7:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወይስ ከእናንተ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው?
ያጋሩ
ማቴዎስ 7 ያንብቡ