ማቴዎስ 7:13-20
ማቴዎስ 7:13-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፤ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ማቴዎስ 7:13-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። “በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ፣ መጥፎም ዛፍ ጥሩ ፍሬ ማፍራት አይችልም። ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህ በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ማቴዎስ 7:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
ማቴዎስ 7:13-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“በጠባብዋ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚያስገባው በር ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነው። ወደዚያ የሚገቡትም ሰዎች ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት የሚያስገባው በር ግን ጠባብ ነው፤ መንገዱም አስቸጋሪ ነው፤ እርሱን የሚያገኙት ሰዎች ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፥ በውስጣቸው ግን እንደ ነጣቂ ተኲላዎች ከሆኑት ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን? እንዲሁም መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፤ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ መጥፎ ዛፍም መልካም ፍሬ ማፍራት አይችልም። መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ፥ ተቈርጦ ወደ እሳት ይጣላል። ስለዚህ፥ ሐሰተኞች ነቢያትን በሥራቸው ፍሬ ታውቁአቸዋላችሁ።
ማቴዎስ 7:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“በጠባብዋ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው በር ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና፤ በዚያም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ጠባብ፥ መንገዱም ቀጭን ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፥ በውስጣቸው ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው። በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬን ያፈራል። መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬን ማፍራት አይችልም፥ መጥፎ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም። መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህ በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።