ማቴዎስ 6:5-13

ማቴዎስ 6:5-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ። እነርሱን አትምሰሏቸው፤ አባታችሁ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃልና። “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን። የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን። እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ፤ መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም ለዘላለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን።’

ማቴዎስ 6:5-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። “አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’

ማቴዎስ 6:5-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወድዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ። እነርሱን አትምሰሏቸው፤ አባታችሁ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃልና። “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ “ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን። የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን። እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉው አድነን እንጂ፤ መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም ለዘላለሙ ያንተ ነውና፤ አሜን።’

ማቴዎስ 6:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።

ማቴዎስ 6:5-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“በምትጸልዩበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ! እነርሱ ሰው እንዲያይላቸው ብለው በየምኲራቡና በየመንገዱ ዳር ቆመው መጸለይ ይወዳሉ። በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን በቅድሚያ አግኝተዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል። “እናንተ ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ ከንቱ ቃል በመደጋገም አትለፍልፉ፤ እነርሱ በመደጋገማቸው ብዛት እግዚአብሔር ጸሎታቸውን የሚሰማቸው ይመስላቸዋል። እናንተ ግን፥ አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ገና ሳትለምኑት አስቀድሞ ስለሚያውቅ እንደ እነርሱ አትሁኑ። ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም በምድር ይሁን። የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን። እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]

ማቴዎስ 6:5-13

ማቴዎስ 6:5-13 NASVማቴዎስ 6:5-13 NASV