ማቴዎስ 3:1-6 - Compare All Versions

ማቴዎስ 3:1-6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። በነቢዩ በኢሳይያስ “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” የተባለለት ይህ ነውና። ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ። ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

ማቴዎስ 3:1-6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚያ ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። ስብከቱም፣ “ንስሓ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና” የሚል ነበር። በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው፤ “በምድረ በዳ፣ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጐዳናውንም አስተካክሉ’ እያለ የሚጮኽ ድምፅ።” የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር። ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣ ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በርሱ እጅ ይጠመቁ ነበር።

ማቴዎስ 3:1-6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። በነቢዩ በኢሳይያስ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና። ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ። ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

ማቴዎስ 3:1-6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚያን ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ በረሓ እየሰበከ መጣ። ሲያስተምርም “እነሆ! የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” ይል ነበር። “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥ ጥርጊያውንም አቅኑ!’ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ ነበር። የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጒር የተሠራ ነበር፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የጣዝማ ማር. ነበር፤ በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም ከመላው የይሁዳ ምድር፥ ከዮርዳኖስም ዙሪያ ሁሉ፥ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር። ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ይጠመቁ ነበር።

ማቴዎስ 3:1-6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። እንዲህም አለ፦ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ።” በነቢዩ በኢሳይያስ “‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና። የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጉር የተሠራ ነበር፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር። በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም፥ ከይሁዳ ሁሉና በዮርዳኖስም ዙሪያ ካሉ አውራጃዎች ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፤ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።