ማቴዎስ 17:14-18
ማቴዎስ 17:14-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ! ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበትክፉኛ ይሣቀያልና፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውሃ ይወድቃልና። ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው፤” አለው። ኢየሱስም መልሶ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት፤” አለ። ኢየሱስም ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።
ማቴዎስ 17:14-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ሕዝቡ እንደ ተመለሱ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ በፊቱ ተንበረከከና እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ እባክህ ልጄን ማርልኝ፤ በሚጥል በሽታ እጅግ እየተሠቃየ ነው፤ ብዙ ጊዜ እሳት ውስጥ ይወድቃል፤ ውሃ ውስጥም ይገባል፤ ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ ነገር ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።” ኢየሱስም፣ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደዚህ አምጡት!” አለ። ከዚያም ኢየሱስ ጋኔኑን ገሠጸውና ከልጁ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነ።
ማቴዎስ 17:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ፦ ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሣቀያልና፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውኃ ይወድቃልና። ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።
ማቴዎስ 17:14-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስና ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ሕዝቡ በተመለሱ ጊዜ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ በእግሩ ሥር ተንበረከከና እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሆይ! እባክህ ለልጄ ራራለት፤ የሚጥል የጋኔን በሽታ ክፉኛ ያሠቃየዋል፤ በእሳት ላይና በውሃ ውስጥ ብዙ ጊዜ ይወድቃል። ወደ ደቀ መዛሙርትህም አምጥቼው ነበር፤ ነገር ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።” ኢየሱስም “እናንተ የማታምኑ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው። ኢየሱስ ጋኔኑን ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከልጁ ወጣ፤ ልጁም በዚያኑ ሰዓት ተፈወሰ።
ማቴዎስ 17:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ወደ ሕዝቡም በመጡ ጊዜ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ! ልጄን ማርልኝ፥ በሚጥል በሽታ ክፉኛ ይሣቀያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ላይ ብዙ ጊዜ ደግሞ በውሃ ውስጥ ይወድቃልና። ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት ነገር ግን ሊፈውሱት አልቻሉም” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “የማያምንና ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት” ኢየሱስም ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።