ማቴዎስ 16:2-4
ማቴዎስ 16:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው “በመሸ ጊዜ ‘ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ። ማለዳም ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፤ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን? ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ትቶአቸውም ሄደ።
ማቴዎስ 16:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ምሽት ላይ፣ ‘ሰማዩ ስለ ቀላ ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤ ንጋት ላይም፣ ‘ሰማዩ ቀልቷል፣ ከብዷልም፤ ስለዚህ ዝናብ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ገጽታ ትለያላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።” ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ሄደ።
ማቴዎስ 16:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በመሸ ጊዜ፦ ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፤ ማለዳም፦ ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን? ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ።
ማቴዎስ 16:2-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ [“በማታ ሰማይ ቀልቶ ስታዩ ‘ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤ ሲነጋ በጠዋት ደግሞ ‘ሰማዩ ደመና ሆኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ፤ የሰማዩንስ መልክ መለየት ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም።] ክፉና የማያምን ትውልድ፥ ምልክት ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።” ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ትቶአቸው ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።