ማቴዎስ 15:7-11
ማቴዎስ 15:7-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል፤’ ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።” ሕዝቡንም ጠርቶ “ስሙ አስተውሉም፤ ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው።
ያጋሩ
ማቴዎስ 15 ያንብቡማቴዎስ 15:7-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እናንተ ግብዞች፤ ኢሳይያስ ስለ እናንተ እንዲህ ብሎ በትንቢት የተናገረው ትክክል ነው፤ “ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በከንቱ ያመልኩኛል፣ ትምህርታቸውም ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።’ ” ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙ፤ አስተውሉም፤ ሰውን የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው እንጂ ወደ አፉ የሚገባው አይደለም።”
ያጋሩ
ማቴዎስ 15 ያንብቡማቴዎስ 15:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፦ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ። ሕዝቡንም ጠርቶ፦ ስሙ አስተውሉም፤ ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው።
ያጋሩ
ማቴዎስ 15 ያንብቡ