ማቴዎስ 10:16-20
ማቴዎስ 10:16-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።
ማቴዎስ 10:16-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“እንግዲህ፣ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ። ሰዎች ይዘው ለፍርድ ወደ ሸንጎ ያቀርቧችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ስለዚህ ከእነርሱ ተጠንቀቁ። በእኔ ምክንያት ወደ ገዦችና ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፤ በእነርሱና በአሕዛብም ፊት ምስክር ትሆናላችሁ። አሳልፈው በሚሰጧችሁ ጊዜ ሁሉ፣ ምን እንናገራለን፣ ምንስ እንመልሳለን ብላችሁ አትጨነቁ፤ በዚያ ጊዜ የምትናገሩት ይሰጣችኋል፤ በእናንተ የሚናገረው የሰማዩ አባታችሁ መንፈስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
ማቴዎስ 10:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።
ማቴዎስ 10:16-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“እነሆ! እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች፥ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ። ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራባቸውም ይገርፉአችኋል፤ ስለዚህ ከሰዎች ተጠንቀቁ። በእኔ ምክንያት፥ ወደ ገዢዎችና ወደ ነገሥታት ለፍርድ ስለምትወሰዱ በእነርሱና በአሕዛብ ፊት ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤ ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ ሲያቀርቡአችሁ የምትናገሩት ነገር በዚያን ሰዓት ስለሚሰጣችሁ፥ ‘እንዴት ወይም ምን እንናገራለን?’ ብላችሁ በማሰብ አትጨነቁ። በእናንተ ውስጥ ዐድሮ የሚናገር የሰማዩ አባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም።
ማቴዎስ 10:16-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ከሰዎች ተጠንቀቁ፥ ምክንያቱም ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና፤ ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ። አሳልፈው በሰጡአችሁ ጊዜ፥ እንዴት ወይም ምን እንደምትናገሩ አትጨነቁ፤ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና፤ በእናንተ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።