ማቴዎስ 1:1-6
ማቴዎስ 1:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።
ማቴዎስ 1:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው። አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ፤ ይሥሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ከረዓብ ወለደ፤ ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።
ማቴዎስ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
ማቴዎስ 1:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የዳዊትና የአብርሃም ዘር የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፦ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳ ፋሬስንና ዛራን ትዕማር ከምትባል ሴት ወለደ፤ ፋሬስ ሔስሮንን ወለደ፤ ሔስሮንም አራምን ወለደ፤ አራም ዓሚናዳብን ወለደ፤ ዓሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ረዓብ ከምትባል ሴት ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ሩት ከምትባል ሴት ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤
ማቴዎስ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ መጽሐፍ። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮም አራምን ወለደ፤ አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።