ሉቃስ 7:11-14
ሉቃስ 7:11-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በማግሥቱም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ሕዝብም አብረውት ሄዱ። ወደ ከተማው በር በደረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያንዲት መበለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳውን ተሸክመው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸውም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙዎችም የከተማ ሰዎች አብረዋት ነበሩ። ጌታችንም በአያት ጊዜ አዘነላትና፥ “አታልቅሺ” አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ያዘ፤ የተሸከሙትም ቆሙ፤ እርሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እልሃለሁ” አለው።
ሉቃስ 7:11-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ብዙ ሳይቈይ፣ ናይን ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብም ዐብረውት ሄዱ። ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከርሷ ጋራ ነበረ። ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት። ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ “አንተ ጐበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ!” አለው።
ሉቃስ 7:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በነገውም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ። ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ። ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና፦ አታልቅሽ አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም፦ አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ።
ሉቃስ 7:11-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በማግስቱ ኢየሱስ ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ፤ ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር። ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና “አይዞሽ፥ አታልቅሺ!” አላት። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደፊት ራመድ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ ቃሬዛውንም የተሸከሙት ሰዎች ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።
ሉቃስ 7:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በማግስቱም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ። ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ አንድ የሞተ ሰው ተሸክመው እያወጡ ነበር፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ነበረ፤ እርሷም መበለት ነበረች፤ የከተማይቱም ብዙ ሕዝብ ከእርሷ ጋር አብረው ነበሩ። ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ቆሙ፤ እርሱም፦ “አንተ ወጣት! ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።