ሉቃስ 5:5-8
ሉቃስ 5:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስምዖንም መልሶ፥ “መምህር፥ ሌሊቱን ሁሉ ደክመናል፤ የያዝነውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘዝኸን መረቦቻችንን እንጥላለን” አለው። እንዳዘዛቸውም ባደረጉ ጊዜ፥ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ ብዙ ዓሣ ተያዘ። መጥተውም ይረዱአቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነበሩትን ባልንጀሮቻቸውን ጠሩ፤ መጥተውም እስኪጠልቁ ድረስ ሁለቱን ታንኳዎች ሞሉ። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።
ሉቃስ 5:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስምዖንም መልሶ፣ “መምህር ሆይ፤ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም ዐድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልህ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። እንደዚያም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረባቸውም ይበጣጠስ ጀመር። በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻቸው መጥተው እንዲያግዟቸውም በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስመጥ ጀመሩ። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፣ “ጌታ ሆይ፤ እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው።
ሉቃስ 5:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው ጠቀሱ፤ መጥተውም ሁለቱ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው።
ሉቃስ 5:5-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስምዖንም “መምህር ሆይ! ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልክ ግን፥ እነሆ! መረቡን እንጥላለን፤” አለው። መረቡን በጣሉ ጊዜ መረቡ እስኪቀደድ ድረስ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው። ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ፊት ተንበርክኮ፥ “ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ ወደ እኔ አትቅረብ!” አለው።
ሉቃስ 5:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው። ይህንም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።