ሉቃስ 4:31-32 - Compare All Versions

ሉቃስ 4:31-32 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ወደ ገሊላ ከተ​ማም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረደ፤ በሰ​ን​በ​ትም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር። አነ​ጋ​ገ​ሩም በት​እ​ዛዝ ነበ​ርና ትም​ህ​ር​ቱን ያደ​ንቁ ነበር።

ሉቃስ 4:31-32 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም በገሊላ አውራጃ ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም በሰንበት ዕለት ሕዝቡን ያስተምር ጀመር፤ የሚናገረው በሥልጣን ስለ ነበር፣ በትምህርቱ ተደነቁ።

ሉቃስ 4:31-32 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ ቃሉ በሥልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ።

ሉቃስ 4:31-32 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከዚህም በኋላ፥ ኢየሱስ በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ፤ በዚያም፥ ሕዝቡን በሰንበት ቀን ያስተምር ነበር። በሥልጣን ቃል ይናገር ስለ ነበር ሁሉም በትምህርቱ ይደነቁ ነበር።

ሉቃስ 4:31-32 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የገሊላ ከተማም ወደ ሆነችው ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ ቃሉ በሥልጣን ተሞልቶ ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ።