ሉቃስ 3:4-6
ሉቃስ 3:4-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በምድረ በዳ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ድምፅ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ቃል እንደ ተጻፈ፥ እንዲህ ሲል፥ “የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፤ ጥርጊያውንም አስተካክሉ። ጐድጓዳው ሁሉ ይምላ፤ ተራራውም፥ ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ሰንከልካላውም የቀና ጥርጊያ ይሁን፤ ወጣ ገባው መንገድም ይስተካከል። ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትድግና ይይ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 3 ያንብቡሉቃስ 3:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይኸውም፣ ነቢዩ ኢሳይያስ በመጽሐፉ እንዲህ ሲል በጻፈው ቃል መሠረት ነበር፤ “በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጐዳናውንም አቅኑ፤ ሸለቆው ሁሉ ይሞላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው መንገድ ቀና፣ ወጣ ገባውም ጐዳና ለጥ ያለ ሜዳ ይሆናል፤ የሰውም ዘር ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።’ ”
ያጋሩ
ሉቃስ 3 ያንብቡሉቃስ 3:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ።
ያጋሩ
ሉቃስ 3 ያንብቡ