ሉቃስ 3:10-14
ሉቃስ 3:10-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡም፥ “እንግዲህ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ።” ቀራጮችም ሊያጠምቃቸው መጡና፥ “መምህር፥ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፥ “ከታዘዛችሁት አትርፋችሁ አትውሰዱ” አላቸው። ጭፍሮችም መጥተው፥ “እኛሳ ምን እናድርግ?” አሉት፤ “በደመወዛችሁ ኑሩ እንጂ በማንም ግፍ አትሥሩ፤ ማንንም አትቀሙ፤ አትበድሉም” አላቸው።
ሉቃስ 3:10-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሕዝቡም፣ “ታዲያ፣ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። ዮሐንስም፣ “ሁለት ልብስ ያለው ምንም ለሌለው ያካፍል፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” ብሎ መለሰላቸው። ቀረጥ ሰብሳቢዎችም ሊጠመቁ ወደ እርሱ መጥተው፣ “መምህር ሆይ፤ እኛስ ምን እናድርግ?” አሉት። እርሱም፣ “ከታዘዛችሁት በላይ ቀረጥ አትሰብስቡ” አላቸው። ወታደሮች ደግሞ፣ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “የማንንም ገንዘብ በግፍ አትንጠቁ፤ ሰውንም በሐሰት አትክሰሱ፤ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ” አላቸው።
ሉቃስ 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሕዝቡም፦ እንግዲህ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። መልሶም፦ ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር። ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት። ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው። ጭፍሮችም ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው።
ሉቃስ 3:10-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሕዝቡም “ታዲያ፥ ምን እናድርግ?” ሲሉ ዮሐንስን ጠየቁት። እርሱም፦ “ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም ለሌለው ያካፍል፤” አላቸው። ቀራጮችም ሊጠመቁ ወደ እርሱ መጥተው “መምህር ሆይ! እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ “በሕግ ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትጠይቁ፤” አላቸው። ወታደሮችም መጥተው፥ “እኛስ ምን እናድርግ?” አሉት፤ እርሱም፦ “የሰው ገንዘብ በግፍ ነጥቃችሁ አትውሰዱ፤ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤ የራሳችሁ ደመወዝ ይብቃችሁ፤” አላቸው።
ሉቃስ 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሕዝቡም፦ “ታድያ፥ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሁለት ልብስ ያለው ምንም ለሌለው ያካፍል፤ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ።” ግብር ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ “መምህር ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉት። እርሱም፦ “ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ ምንም አትሰብስቡ፤” አላቸው። ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።