ሉቃስ 24:9-12
ሉቃስ 24:9-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከመቃብርም ተመልሰው ለዐሥራ አንዱና ለቀሩት ባልንጀሮቻቸው ሁሉ ይህን ነገር ነገሩአቸው። እነዚያም መግደላዊት ማርያም፥ ዮሐና፥ የያዕቆብ እናት ማርያም፥ አብረዋቸው የነበሩት ባልንጀሮቻቸውም ይህን ለሐዋርያት ነገሩአቸው። ይህም ነገር በፊታቸው እንደ ተረት መሰላቸውና አላመኑአቸውም። ጴጥሮስም ተነሣ፤ ወደ መቃብርም ፈጥኖ ሄደ፤ ዝቅ ብሎም በተመለከተ ጊዜ በፍታውን ለብቻው ተቀምጦ አየ፤ የሆነውንም እያደነቀ ተመለሰ።
ሉቃስ 24:9-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሴቶቹ ከመቃብሩ ስፍራ ተመልሰው ይህን ሁሉ ነገር ለዐሥራ አንዱና ለተቀሩት ሁሉ ነገሯቸው። ይህን ለሐዋርያት የነገሯቸውም፣ መግደላዊት ማርያም፣ ዮሐና፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ከእነርሱ ጋራ የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ። እነርሱ ግን ሴቶቹ የተናገሩት ቃል መቀባዠር ስለ መሰላቸው አላመኗቸውም። ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ እዚያ ደርሶም ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ በፍታውን ብቻ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተገረመ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
ሉቃስ 24:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ቃሎቹንም አሰቡ፥ ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለአሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው። ይህንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና የያዕቆብም እናት ማርያም ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ። ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም። ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብር ሮጠ፤ በዚያም ዝቅ ብሎ ሲመለከት የተልባ እግር ልብስን ብቻ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤቱ ሄደ።
ሉቃስ 24:9-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከመቃብርም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለቀሩትም ነገሩአቸው። ይህን ለሐዋርያት የተናገሩት መግደላዊት ማርያም፥ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም፥ እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ነበሩ። እነርሱ ግን ይህ ነገር ቅዠት ስለ መሰላቸው አላመኑአቸውም። ነገር ግን ጴጥሮስ ተነሥቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ እዚያም ሲደርስ ጐንበስ ብሎ በተመለከተ ጊዜ አስከሬኑ የተከፈነበትን ቀጭን የሐር ልብስ ለብቻ ተቀመጦ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤት ተመለሰ።
ሉቃስ 24:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው። ይህንንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና፥ የያዕቆብም እናት ማርያም፥ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የነበሩ ሌሎች ሴቶች ነበሩበት። ነገር ግን ይህ ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም። ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብር ሮጠ፤ በዚያም ዝቅ ብሎ ሲመለከት ቀጭን የሐር ልብስ ለብቻ ተቀምጦ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤቱ ሄደ።