ሉቃስ 21:8 - Compare All Versions
ሉቃስ 21:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ፤ ጊዜውም ደርሶአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና እንዳያስቱአችሁ ተጠንቀቁ፤ እነርሱንም ተከትላችሁ አትሂዱ።
ሉቃስ 21:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች፣ ‘እኔ እርሱ ነኝ’ በማለት፣ ደግሞም፣ ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እናንተ ግን እነርሱን አትከተሏቸው።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 NASVሉቃስ 21:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እንዲህም አለ፦ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች፦ እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 አማ54ሉቃስ 21:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 አማ05ሉቃስ 21:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እንዲህም አለ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች ‘እኔ ነኝ፤ ዘመኑም ቀርቦአል፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።
ያጋሩ
ሉቃስ 21 መቅካእኤ