ሉቃስ 15:25-28
ሉቃስ 15:25-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ታላቁ ልጁም በእርሻ ነበርና ተመልሶ ወደ ቤቱ አጠገብ በደረሰ ጊዜ የዘፈኑንና የመሰንቆውን ድምፅ ሰማ። ከአባቱ ብላቴኖችም አንዱን ጠርቶ፦ ‘ይህ የምሰማው ምንድን ነው?’ አለው። እርሱም፦ ‘ወንድምህ ከሄደበት መጣ፤ አባትህም የሰባውን ፍሪዳ አረደ፤ በሕይወት አግኝቶታልና’ አለው። ተቈጥቶም ‘አልገባም’ አለ፤ አባቱም ወጥቶ ማለደው።
ሉቃስ 15:25-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ፤ ከዚያም ተመልሶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ፣ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤ እርሱም ከብላቴኖቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደ ሆነ ጠየቀው። አገልጋዩም፣ ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በሰላም በጤና ስለ መጣም አባትህ የሠባውን ፍሪዳ ዐርዶለታል’ አለው። “ታላቅ ወንድሙም ተቈጣ፤ ወደ ቤትም መግባት አልፈለገም፤ አባቱም ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲገባ ለመነው።
ሉቃስ 15:25-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ታላቁ ልጁ በእርሻ ነበረ፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የመሰንቆና የዘፈን ድምፅ ሰማ፤ ከብላቴናዎችም አንዱን ጠርቶ፦ ይህ ምንድር ነው? ብሎ ጠየቀ። እርሱም፦ ወንድምህ መጥቶአልና በደኅና ስላገኘው አባትህ የሰባውን ፊሪዳ አረደለት አለው። ተቈጣም ሊገባም አልወደደም፤ አባቱም ወጥቶ ለመነው።
ሉቃስ 15:25-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ ለሥራ ወደ እርሻ ወጥቶ ነበር፤ ተመልሶ ሲመጣ ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ‘ምንድን ነው ነገሩ?’ ብሎ ጠየቀው። አገልጋዩም ‘ወንድምህ ተመልሶ ስለ መጣ ነው፤ አባትህ በደኅና ስላገኘው የሰባውን ወይፈን ዐርዶለታል’ አለው። “ታላቅ ወንድሙም በጣም ተቈጥቶ፥ ‘ወደ ቤት አልገባም’ አለ። ስለዚህ አባቱ ወደ ደጅ ወጥቶ እንዲገባ ለመነው፤