ሉቃስ 13:34-35
ሉቃስ 13:34-35 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ነቢያትን የምትገድሊያቸው፥ ወደ አንቺ የተላኩትን ሐዋርያትንም የምትደበድቢያቸው ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፍዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስባቸው ምን ያህል ወደድሁ? ነገር ግን እንቢ አላችሁ። እነሆ፥ ቤታችሁ ምድረ በዳ ሆኖ ይቀርላችኋል፤ ከዛሬ ወዲያ ‘በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው’ እስክትሉ ድረስ እንደማታዩኝ እነግራችኋለሁ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 13 ያንብቡሉቃስ 13:34-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤ እነሆ፤ ቤታችሁ ወና ሆኖ ቀርቷል። እላችኋለሁ፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ አታዩኝም።”
ያጋሩ
ሉቃስ 13 ያንብቡሉቃስ 13:34-35 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፥ እናንተም አልወደዳችሁም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁም፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።
ያጋሩ
ሉቃስ 13 ያንብቡ