ሉቃስ 13:25 - Compare All Versions
ሉቃስ 13:25 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ባለቤቱ ተነሥቶ ደጁን ይዘጋልና፤ ያንጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈትልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀምራሉ፤ መልሶም፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላቸዋል።
ሉቃስ 13:25 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደ ሆናችሁና ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።
ያጋሩ
ሉቃስ 13 NASVሉቃስ 13:25 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላችኋል።
ያጋሩ
ሉቃስ 13 አማ54ሉቃስ 13:25 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
ያጋሩ
ሉቃስ 13 አማ05ሉቃስ 13:25 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።
ያጋሩ
ሉቃስ 13 መቅካእኤ