ሉቃስ 10:39-42
ሉቃስ 10:39-42 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች። ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው። ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።
ሉቃስ 10:39-42 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ማርያም የምትባል እኅትም ነበረቻት፤ እርስዋም ከጌታችን ኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ትምህርቱን ትሰማ ነበር። ማርታ ግን ብዙ በማዘጋጀት ትደክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻዬን ስሠራ አያሳዝንህምን? ርጃት በላት” አለችው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደክሚያለሽ፥ ትቸገሪያለሽም፤ ታዘጋጂያለሽም። ጥቂት ይበቃል፤ ያም ባይሆን አንድ ይበቃል፤ ማርያምስ የማይቀሙአትን መልካም ዕድል መረጠች።”
ሉቃስ 10:39-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሷም ማርያም የተባለች እኅት ነበረቻት፤ ማርያምም ቃሉን እየሰማች በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ ነበር። ማርታ ግን በሥራ ብዛት ትባክን ነበርና ወደ እርሱ ቀርባ፣ “ጌታ ሆይ፤ እኅቴ ሥራውን ለእኔ ብቻ ጥላ ስትቀመጥ ዝም ትላለህን? እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው። ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከርሷ አይወሰድም።”
ሉቃስ 10:39-42 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች። ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው። ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።
ሉቃስ 10:39-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርስዋ ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ ይህች ማርያም በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ትምህርቱን ታደምጥ ነበር። ማርታ ግን ምግብ በማዘጋጀት በብርቱ ትደክም ነበር፤ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ቀርባ፥ “ጌታ ሆይ! ይህች እኅቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህን? እባክህ እንድታግዘኝ ንገራት!” አለችው። ጌታ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ማርታ፥ ማርታ፥ አንቺ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪያለሽም፤ ነገር ግን ተፈላጊው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም የሚሻለውን ነገር መርጣለች፤ እርሱንም ከእርስዋ የሚወስድባት ማንም የለም።”
ሉቃስ 10:39-42 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ እርሷም ደግሞ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ቃሉን ትሰማ ነበር። ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ “ጌታ ሆይ! እኅቴ ብቻዬን እንዳገለግል ስትተወኝ አይገድህምን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት፤” አለችው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ! ማርታ! በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪያለሽም፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያምም መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ከእርሷም አይወሰድባትም።”