ሉቃስ 10:19-20
ሉቃስ 10:19-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጐዳችሁም ነገር የለም። ነገር ግን አጋንንት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ግን ስማችሁ በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 10 ያንብቡሉቃስ 10:19-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ እባቡንና ጊንጡን እንድትረግጡ፣ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጐዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም። ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
ያጋሩ
ሉቃስ 10 ያንብቡሉቃስ 10:19-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
ያጋሩ
ሉቃስ 10 ያንብቡ