ሉቃስ 1:1-7

ሉቃስ 1:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው። ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤ የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ። የተ​ማ​ር​ኸ​ውን የነ​ገ​ሩን እው​ነት ጠን​ቅ​ቀህ ታውቅ ዘንድ። በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ። ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ። ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።