ዘሌዋውያን 9:1-7

ዘሌዋውያን 9:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠራ። ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፦ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ልን፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ዓመት የሆ​ና​ቸ​ውን ጥጃና ጠቦ​ትን፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ንና አውራ በግን፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ልና ብለህ ንገ​ራ​ቸው።” ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ። ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ። ሙሴም አሮ​ንን፥ “ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀር​በህ የኀ​ጢ​አ​ት​ህን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ሠዋ፤ ለራ​ስ​ህና ለወ​ገ​ንህ አስ​ተ​ስ​ርይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘዘ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቅ​ርብ፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም” አለው።

ዘሌዋውያን 9:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራቸው። አሮንንም እንዲህ አለው፤ “የኀጢአት መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ እንቦሳ እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆንልህ አንድ አውራ በግ ወስደህ፣ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ ሁለቱም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ። እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፤ ‘ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት እንከን የሌለባቸውን የአንድ ዓመት እንቦሳና የአንድ ዓመት ጠቦት፣ ለኅብረት መሥዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቍርባን ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ” እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ሕዝቡም በሙሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። ሙሴም፣ “የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥላችሁ ዘንድ፣ እንድታደርጉት እግዚአብሔር ያዘዛችሁ ይህ ነው” አለ። ሙሴ አሮንን፣ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአት መሥዋዕትህንና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት የሕዝቡን መሥዋዕት አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው።

ዘሌዋውያን 9:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። አሮንንም አለው፦ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እምቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ነውር የሌለባቸውን ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው። የእስራኤልንም ልጆች፦ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ ብለህ ንገራቸው። ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። ሙሴም፦ ታደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥላችኋል አለ። ሙሴም አሮንን፦ ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም አለው።

ዘሌዋውያን 9:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሰባት ቀን የቈየው የክህነት አሰጣጥ ሹመት በተፈጸመ ማግስት ሙሴ አሮንንና ልጆቹን፥ እንዲሁም የእስራኤልን መሪዎች ጠራ፤ አሮንንም እንዲህ አለው፤ “ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ የበግ አውራ ወስደህ ወይፈኑን ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ የበግ አውራውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርብ። ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል፥ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ጥጃና የአንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያመጡ ንገራቸው። እንዲሁም አንድ ወይፈንና አንድ የበግ ጠቦት ለአንድነት መሥዋዕት ያምጡ፤ እነዚህንም በዘይት ከታሸ የእህል መባ ጋር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ስለሚገለጥላቸው ይህን ሁሉ ያድርጉ።” እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ወደዚያ ተጠግተው ቆሙ። ሙሴም “የእግዚአብሔር ክብር ስለሚገለጥላችሁ ይህን ሁሉ እንድታደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።” አላቸው። ከዚህም በኋላ ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፤ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የራስህን ኃጢአትና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርበውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ፤ ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አቅርብ።”

ዘሌዋውያን 9:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። አሮንንም እንዲህ አለው፦ “ከመንጋው ነውር የሌለባቸውን ለኃጢአት መሥዋዕት እምቦሳውን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ወስደህ በጌታ ፊት አቅርብ። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፦ ‘ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥ ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ” ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በጌታ ፊት ቆሙ። ሙሴም፦ “የጌታም ክብር እንዲገለጥላችሁ ጌታ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህን ነገር ነው፤” አለ። ሙሴም አሮንን፦ “ወደ መሠዊያው ቅረብ፥ የኃጢአትህንም መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ ጌታም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም” አለው።