ኢያሱ 7:20-21
ኢያሱ 7:20-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አካንም መልሶ ኢያሱን፥ “በእውነት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት በድያለሁ፤ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ። በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፤ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።
ኢያሱ 7:20-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እውነት ነው! የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ፤ ያደረግሁትም ይህ ነው፤ ከምርኮው ዕቃ መካከል ከሰናዖር የመጣ አንድ የሚያምር ካባ፣ ሁለት መቶ ሰቅል ብርና ክብደቱ ዐምሳ ሰቅል የሚሆን የወርቅ ቡችላ አይቼ ጐመጀሁ፤ ወሰድኋቸውም፤ ዕቃውም ብሩ ከታች ሆኖ፣ በድንኳኔ ውስጥ መሬት ተቀብሯል።”
ኢያሱ 7:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አካንም መልሶ ኢያሱን፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ። በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም፥ እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው።
ኢያሱ 7:20-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዓካንም እንዲህ ሲል መለሰ፥ “እውነት ነው፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የበደልኩ እኔ ነኝ፤ እነሆ፥ ያደረግኹትም ከዚህ የሚከተለው ነው፤ ካገኘነው ዕቃ መካከል ውብ የሆነ የባቢሎናውያን ካባ፥ ሁለት ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብርና ግማሽ ኪሎ ያህል የሚመዝን ምዝምዝ ወርቅ አየሁ፤ እነርሱንም ለማግኘት ብርቱ ፍላጎት ስላደረብኝ ወስጃቸዋለሁ፤ እነርሱንም ብሩ ከታች ሆኖ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተቀብረዋል።”