ኢያሱ 7:16-18
ኢያሱ 7:16-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው ሰበሰባቸው፤ በይሁዳም ነገድ ላይ ምልክት ታየ፤ የይሁዳም ወገኖች ተለዩ፤ በዛራም ወገን ምልክት ታየ፤ የዛራም ወገን በየቤተ ሰቡ ተለየ፤ በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ።
ያጋሩ
ኢያሱ 7 ያንብቡኢያሱ 7:16-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገድ በየነገዳቸው ሆነው እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ ተለየ። የይሁዳንም ጐሣዎች ወደ ፊት አቀረበ፤ ከእነዚህም የዛራን ጐሣ ለየ፤ እነዚህን ደግሞ በየቤተ ሰባቸው እንዲወጡ አደረገ፤ ከእነዚህም ዘንበሪ ተለየ። ኢያሱ የዘንበሪን ቤተ ሰብ አባላት አንድ በአንድ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የሆነውም የዛራ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የከርሚ ልጅ አካን ለብቻው ተለየ።
ያጋሩ
ኢያሱ 7 ያንብቡኢያሱ 7:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፥ የይሁዳም ነገድ ተለየ፥ የይሁዳንም ወገን አቀረበ የዛራንም ወገን ለየ፥ የዛራንም ወገን ሰዎች አቀረበ፥ ዘንበሪም ተለየ፥ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ፥ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።
ያጋሩ
ኢያሱ 7 ያንብቡ