ኢያሱ 6:8-9
ኢያሱ 6:8-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በእግዚአብሔርም ፊት ይሄዱ ዘንድ ኢያሱ እንደ ነገራቸው ሰባቱ ካህናት የተቀደሱ ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው ሄዱ፤ በሄዱም ጊዜ አሰምተው በምልክት ነፉ፤ የእግዚአብሔርም የሕጉ ታቦት ትከተላቸው ነበር። ሰልፈኞችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህናቱም ነጋሪት ይመቱ ነበር፤ ከታቦቱ በኋላ ይከተሉ የነበሩትም ቀንደ መለከቱን እየነፉ ይሄዱ ነበር።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡኢያሱ 6:8-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢያሱም ለሕዝቡ ከተናገረ በኋላ፣ ሰባቱ ካህናት በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው መለከታቸውን እየነፉ ወደ ፊት ቀደሙ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ተከተላቸው። የታጠቁ ተዋጊዎችም መለከት ከሚነፉት ካህናት ፊት ቀድመው ሲሄዱ፣ ደጀን የሆኑት ጠባቂዎች ደግሞ ታቦቱን ተከተሉ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ መለከቶቹ ባለማቋረጥ ይነፉ ነበር።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡኢያሱ 6:8-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢያሱም ለሕዝቡ በተናገረ ጊዜ፥ ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ፊት ሄዱ ቀንደ መለከቱንም ነፉ፥ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ይከተላቸው ነበር። ሰልፈኞቹም ቀንደ መለከቱን በሚነፉ በካህናቱ ፊት ይሄዱ ነበር፥ የቀረውም ሕዝብ ከታቦቱ በኋላ ይሄድ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡ