ኢያሱ 6:6-7
ኢያሱ 6:6-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። ሕዝቡንም፥ “ሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ፤ ተዋጊዎችም ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላችሁ እዘዙአቸው” አላቸው።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡኢያሱ 6:6-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባት ካህናትም ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡኢያሱ 6:6-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው። ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ ሰልፈኞችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።
ያጋሩ
ኢያሱ 6 ያንብቡ