ኢያሱ 6:22-25

ኢያሱ 6:22-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢያ​ሱም ምድ​ሪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለ​ቱን ሰዎች፥ “ወደ ዘማ​ዪቱ ቤት ግቡ፤ ከዚ​ያም ሴቲ​ቱ​ንና ያላ​ትን ሁሉ እን​ደ​ማ​ላ​ች​ሁ​ላት አውጡ” አላ​ቸው። እነ​ዚ​ያም ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለቱ ጐል​ማ​ሶች ወደ ዘማ​ዪቱ ረዓብ ቤት ገብ​ተው ረዓ​ብን፥ አባ​ቷ​ንና እና​ቷን፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ዋ​ንም፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ፥ ቤተ ዘመ​ዶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በውጭ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው። ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ ነገር ግን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የና​ሱ​ንና የብ​ረ​ቱ​ንም ዕቃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ። ኢያ​ሪ​ኮን ሊሰ​ልሉ ኢያሱ የላ​ካ​ቸ​ው​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊ​ቱን ረዓ​ብን፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤተ ሰብ፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ ኢያሱ አዳ​ና​ቸው፤ እር​ስ​ዋም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጣ​ለች።