ኢያሱ 5:11-12
ኢያሱ 5:11-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከምድሪቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚያው ቀን በሉ። በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ዳግመኛ መና አላገኙም፤ በዚያው ዓመት የፊኒቆንን ምድር ፍሬ ሰበሰቡ።
ያጋሩ
ኢያሱ 5 ያንብቡኢያሱ 5:11-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ። የምድሪቱን ፍሬ በበሉበት ቀን መናው መውረዱ ቀረ፤ ከዚያ በኋላ ለእስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።
ያጋሩ
ኢያሱ 5 ያንብቡኢያሱ 5:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ። በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፥ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፥ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።
ያጋሩ
ኢያሱ 5 ያንብቡ