ኢያሱ 5:1-15

ኢያሱ 5:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ። በዚ​ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን፥ “ከሻፎ ድን​ጋይ የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠር​ተህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዳግ​መኛ ግረ​ዛ​ቸው” አለው። ኢያ​ሱም የባ​ል​ጩት መቍ​ረጫ ሠርቶ የግ​ር​ዛት ኮረ​ብታ በተ​ባለ ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ገረዘ። ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር። ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር። ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ አስ​ነሣ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ኢያሱ ገረ​ዛ​ቸው፤ በመ​ን​ገድ ስለ​ተ​ወ​ለዱ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና። በተ​ገ​ረ​ዙም ጊዜ እስ​ኪ​ድኑ ድረስ በሰ​ፈር ውስጥ ተቀ​መጡ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ። ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ። በነ​ጋ​ውም ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዳግ​መኛ መና አላ​ገ​ኙም፤ በዚ​ያው ዓመት የፊ​ኒ​ቆ​ንን ምድር ፍሬ ሰበ​ሰቡ። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢ​ያ​ሪኮ አጠ​ገብ ሳለ ዐይ​ኑን አን​ሥቶ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ የተ​መ​ዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያ​ሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ወገን ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ኢያ​ሱን፥ “አንተ የቆ​ም​ህ​በት ስፍራ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ” አለው። ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ።

ኢያሱ 5:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ያሉት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፣ በባሕሩም ዳርቻ ያሉ የከነዓናውያን ነገሥታት በሙሉ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን እስክንሻገር ወንዙን በእስራኤላውያን ፊት እንዴት እንዳደረቀው በሰሙ ጊዜ፣ ልባቸው በፍርሀት ቀለጠ፤ እስራኤላውያንንም ለመቋቋም ድፍረት ዐጡ። በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። ስለዚህ ኢያሱ የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅቶ በጊብዓዝ ዓረሎት በተባለ ስፍራ እስራኤላውያንን ገረዛቸው። እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ። ከዚያ የወጡት ሰዎች ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በጕዞ ላይ ሳሉ የተወለዱት ግን በሙሉ አልተገረዙም ነበር። ግብጽን ለቅቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና። ስለዚህ በእነርሱ ምትክ ወንዶች ልጆቻቸውን አስነሣ። እንግዲህ ኢያሱ የገረዛቸው እነዚህን ነበር፤ በጕዞ ላይ ሳሉ ባለመገረዛቸው ከነሸለፈታቸው ነበሩና። ሕዝቡ ሁሉ ከተገረዙ በኋላ ቍስሉ እስኪሽር ድረስ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ቈዩ። ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነሆ፤ ዛሬ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ከዚህም የተነሣ የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተባለ። እስራኤላውያን በኢያሪኮ ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፣ ወሩ በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ። ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ። የምድሪቱን ፍሬ በበሉበት ቀን መናው መውረዱ ቀረ፤ ከዚያ በኋላ ለእስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ። ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ፣ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ። ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፤ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ በመሆኔ እነሆ፤ መጥቻለሁ” ሲል መለሰለት፤ ኢያሱም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፣ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው። የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃም ኢያሱን፣ “ጫማህን ከእግርህ አውልቅ፤ የቆምህባት ምድር የተቀደሰች ናትና” አለው፤ ኢያሱም እንደ ታዘዘው አደረገ።

ኢያሱ 5:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንዲህም ሆነ፥ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነግሥታት ሁሉ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩት ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ነፍስ ከዚያ ወዲያ አልቀረላቸውም። በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፦ የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው አለው። ኢያሱም የባልጩት መቁረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ። ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነው፥ ከግብፅ የወጡት ሕዝብ ወንዶች ሰልፈኞች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ። የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፥ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ሰልፈኞች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር። ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፥ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና። ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተገረዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ተቀመጡ። እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፥ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ። የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፥ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ። በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፥ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፥ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ። እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፥ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው። እርሱም፦ አይደለሁም፥ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው። የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።

ኢያሱ 5:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያሉ የአሞራውያን ነገሥታትና በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ ጠረፉን ተከትለው የሚኖሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ ውሃ እንዳደረቀላቸው በሰሙ ጊዜ፤ በፍርሃት ልባቸው ቀለጠ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን ለመቋቋም ድፍረት አጡ። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን “ከባልጩት የተሠራ መቊረጫ አዘጋጅተህ እስራኤላውያንን እንደገና ግረዛቸው” አለው። ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማድረግ “የግዝረት ኮረብታ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እስራኤላውያንን ገረዘ። ኢያሱ እነርሱን የገረዘበት ምክንያት ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች ሁሉ በበረሓው ጒዞ ጊዜ ሞተው ስለ ነበረ ነው። በመጀመሪያ ከግብጽ ምድር የወጡት ወንዶች ሁሉ ተገርዘው የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በበረሓው ጒዞ ጊዜ የተወለዱት ወንዶች አልተገረዙም ነበር። ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር። ኢያሱ የገረዛቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ቦታ ያስነሣቸውን ልጆቻቸውን ነው፤ እነርሱ በጉዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ስላልተገረዙ ሸለፈታሞች ነበሩ። ሰዎች ሁሉ ከተገረዙ በኋላ ቊስላቸው እስኪድን ድረስ በሰፈር ቈዩ። እግዚአብሔር ኢያሱን፦ “እነሆ፥ ዛሬ እኔ ከእናንተ ላይ የግብጽን ነውር አስወግጄላችኋለሁ” አለው። ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጌልጌላ ተብሎ ይጠራል። እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ ባለው ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፥ ከወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት የጀመሩትም በዚያን ቀን ማግስት ነበር፤ የተመገቡትም የተጠበሰ እሸትና ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ነበር። ከምድሪቱ የሚገኘውን ምግብ መብላት ከጀመሩበት ቀን አንሥቶ መና መዝነቡን አቋረጠ፤ እስራኤላውያንም ከዚያን በኋላ ያን መና ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያን ጊዜ አንሥቶ በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት ጀመሩ። ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ሰይፍ የያዘ አንድ ጐልማሳ በድንገት በፊቱ ቆሞ ታየው፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “አንተ የእኛ ወገን ነህ ወይስ የጠላቶቻችን?” አለው። ጐልማሳውም “የእናንተም ሆነ የጠላት ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥ እንደ መሆኔ መጠን እነሆ፥ መጥቻለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ መሬት ወድቆ ሰገደለትና “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ምን ልታዘዝ?” አለው። የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥም “የቆምክባት ምድር የተቀደሰች ስለ ሆነች ጫማህን አውልቅ” አለው፤ ኢያሱም እርሱ እንዳዘዘው አደረገ።

ኢያሱ 5:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነግሥታት ሁሉ፥ ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩት ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ከዚያ ወዲያ ሐሞተ ቢስ ሆኑ። በዚያን ጊዜም ጌታ ኢያሱን፦ “የባልጩት መቁረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። ኢያሱም የባልጩት መቁረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ። ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነበር፤ ከግብጽ ከወጣው ሕዝብ መካከል ወንዶች ተዋጊዎች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞተው ስለ ነበረ ነው። የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ የተወለዱት ልጆች ሁሉ አልተገረዙም ነበር። ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር። ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፤ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና። ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተገረዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ተቀመጡ። ጌታም ኢያሱን፦ “ዛሬ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ። የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ። በማግስቱም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ። እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው። እርሱም፦ “አይደለሁም፤ እኔ የጌታ ሠራዊት አዣዥ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ “ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድነው?” አለው። የጌታም ሠራዊት አዣዥ ኢያሱን፦ “አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።