ኢያሱ 3:14-17

ኢያሱ 3:14-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊሻ​ገሩ ከየ​ድ​ን​ኳ​ና​ቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር። እንደ ክረ​ም​ትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮር​ዳ​ኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበ​ርና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦ​ቱን የተ​ሸ​ከ​ሙት የካ​ህ​ናቱ እግ​ሮች በው​ኃዉ ዳር ሲጠ​ልቁ፥ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።