ኢያሱ 3:10-13
ኢያሱ 3:10-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢያሱም አለ፥ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው በዚህ ታውቃላችሁ። እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊታችሁ ዮርዳኖስን ትሻገራለች። አሁንም ከእስራኤል ነገዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮርዳኖስ ውኃ ይደርቃል፤ ከላይ የሚወርደውም ውኃ ይቆማል።”
ኢያሱ 3:10-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ መሆኑንና እርሱም በርግጥ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ኤዊያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ እንዴት አድርጎ እንደሚያሳድዳቸው የምታውቁት በዚህ ነው። እነሆ፤ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል። እንግዲህ ከእስራኤል ነገዶች ዐሥራ ሁለት ሰው ምረጡ፤ ከየነገዱም አንዳንድ ሰው ይሁን። የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ገና እግራቸውን በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ እንዳስገቡ፣ ቍልቍል የሚወርደው ውሃ ወዲያውኑ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”
ኢያሱ 3:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢያሱም አለ፦ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈፅሞ እንዲያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ። እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል። አሁንም ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጡ፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። እንዲህም ይሆናል፥ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፥ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።
ኢያሱ 3:10-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢያሱም ንግግሩን በመቀጠል፦ “ሕያው እግዚአብሔር በመካከላችሁ መሆኑን የምታውቁት እናንተ ወደ ፊት እየገፋችሁ በሄዳችሁ መጠን እርሱ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ሒዋውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ የሚያስወጣ በመሆኑ ነው። የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ቀድሞ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ይሸጋገራል። እነሆ፥ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ተወካይ በማቅረብ አሁኑኑ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች ውሃውን በሚነኩበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን ያቆማል፤ ከላይ እየጐረፈ የሚመጣውም ውሃ በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ይቈለላል።”
ኢያሱ 3:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደሆነ፥ እርሱም ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈፅሞ እንደሚያሳድድ በዚህ ታውቃላችሁ። እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል። እንግዲህ አሁን ከእስራኤል ነገዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ምረጡ። እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የጌታን ታቦት የተሸከሙ ካህናት የእግሮቻቸው ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”