ኢያሱ 20:1-9

ኢያሱ 20:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ በሙሴ ቃል የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ስጡ። ባለ​ማ​ወቅ ሳይ​ወ​ድድ ሰውን የገ​ደለ በዚያ ይማ​ፀን ዘንድ፥ ለእ​ና​ንተ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ሥሩ፤ ነፍስ የገ​ደለ ሰውም በአ​ደ​ባ​ባይ ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቀ​ርብ ድረስ በደም ተበ​ቃዩ አይ​ገ​ደል። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ይማ​ፀ​ናል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነገ​ሩን ይና​ገ​ራል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ያገ​ቡ​ታል። የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ስፍራ ይሰ​ጡ​ታል። ባለ ደሙ ቢያ​ሳ​ድ​ደው፥ አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ጠ​ላው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ሕ​ተት ስለ ገደ​ለው ነፍሰ ገዳ​ዩን በእጁ አሳ​ል​ፈው አይ​ስ​ጡት። በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቆም ድረስ ፥ በዚ​ያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚ​ያች ከተማ ይቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ ከተ​ማ​ውም፥ ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣ​በ​ትም ከተማ ይገ​ባል።” በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ። በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ። በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።

ኢያሱ 20:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “በሙሴ በኩል በነገርኋችሁ መሠረት የመማፀኛ ከተሞች እንዲለዩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ ሳያስበው ድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ወደዚያ በመሸሽ ከደም ተበቃዩ እንዲያመልጥ ከተማዪቱ መጠለያ ትሁን። ገዳዩ ከነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በሚሸሽበት ጊዜ፣ በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ቆሞ ጕዳዩን ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ይንገራቸው፤ ከዚያም እነርሱ ወደ ከተማቸው አስገብተው የሚኖርበትን ስፍራ ሰጥተውት ዐብሯቸው ይቀመጥ። ደም ተበቃዩ ተከታትሎት ቢመጣ፣ ሆነ ብሎና በክፋት ተነሣሥቶ ወንድሙን የገደለው ባለመሆኑ፣ ሰዎቹ ነፍሰ ገዳዩን አሳልፈው አይስጡት። በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቀርብና በዚያ ጊዜ የሚያገለግለው ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቈይ። ከዚያም ወደ ቤቱ፣ ሸሽቶ ወደ መጣበት ከተማ ሊመለስ ይችላል።” ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ። እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ። ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም።

ኢያሱ 20:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ሳይወድድ ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፥ ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል። ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፥ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል። ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን በስሕተት ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፥ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል። በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ። በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ። በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

ኢያሱ 20:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፥ እንዲህ አለው፤ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “በሙሴ አማካይነት ባዘዝኳችሁ መሠረት የመማጠኛ ከተሞችን ለዩ፤ ማንም ሰው ሳያውቅ በድንገት ሰው ቢገድል፥ ወደዚያ በመሄድ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው ይድናል፤ እርሱም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ፈጥኖ በመሄድ በከተማይቱ መግቢያ በር ወደሚገኘው ፍርድ ሸንጎ ቀርቦ የሆነውን ነገር ሁሉ ለመሪዎቹ ይገልጣል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ከተማይቱ እንዲገባ ይፈቅዱለታል፤ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡትና በዚያ ይቈያል፤ ሊበቀለው የሚፈልገው ሰው ቢያሳድደው፥ ሰውን የገደለው በድንገተኛ አጋጣሚ እንጂ በቂም በቀል ተነሣሥቶ ስላይደለ የከተማይቱ ሰዎች እርሱን አሳልፈው መስጠት አይገባቸውም፤ በሸንጎ ቀርቦ ፍርድ እስከሚቀበልና በዘመኑ ያለው ሊቀ ካህናት እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ በዚያች ከተማ ሊቈይ ይችላል፤ ከዚያም በኋላ ሸሽቶ ወደወጣበት ከተማ በመመለስ ወደ ቤቱ ይገባል።” ስለዚህም የንፍታሌም ይዞታ በሆነችው በኮረብታማዋ ምድር በምትገኘው በገሊላ፥ ቄዴሽ ተብላ የምትጠራውን፥ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሴኬምንና በኮረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለው ቂርያት አርባቅን መርጠው ለዩ፤ በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤ ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል።

ኢያሱ 20:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘በሙሴ አማካይነት የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፤ እነዚህም ከተሞች በስሕተት ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል። ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል ከእነርሱም ጋር ይቀመጣል። ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን ሳያውቅ ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል።’ ” በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ። በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ። በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።