ኢያሱ 15:1-12
ኢያሱ 15:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የይሁዳም ነገድ ድንበር በየወገናቸው ከኤዶምያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው። በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስከሚወስደው መንገድ ነበረ። ከዚያም በአቅረቢን ዐቀበት ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጺንም ይወጣል፤ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወጣል፤ በአስሮንም በኩል ያልፋል፤ ወደ ሰራዳም ይወጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕራብም ይዞራል። ወደ አጽሞንም ያልፋል፤ በግብፅም ሸለቆ በኩል ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤ ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤ ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወጣል፤ ድንበሩም በሰሜን በኩል በራፋይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባሕር በኩል ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ይወጣል፤ ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል። ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል። ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። በባሕር በኩል ያለው ድንበራቸውም እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
ኢያሱ 15:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል። የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤ ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን ዐልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤ በዓጽሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል። እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው ይህ ነው። በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል። በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና ሽቅብ ወደ ቤትሖግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜናዊው ቤትዓረባ በኩል አድርጎ የሮቤል ልጅ የቦሀን ድንጋይ እስካለበት ይደርሳል። ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል። እንደዚሁም የሄኖምን ልጅ ሸለቆ ዐልፎ ይሄድና የኢያቡሳውያን ከተማ እስከ ሆነችው እስከ ኢየሩሳሌም ደቡባዊ ተረተር በመዝለቅ፣ በራፋይም ሸለቆ ሰሜን ጫፍ በኩል አድርጎ ከሄኖም ሸለቆ በስተ ምዕራብ ካለው ኰረብታ ዐናት ላይ ይደርሳል። ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል። ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል። ደግሞም በአቃሮን ሰሜናዊ ተረተር አድርጎ ወደ ሽክሮን ይታጠፍና በበኣላ ተራራ ላይ ዐልፎ እስከ የብኒኤል ይደርሳል፤ ከዚህ በኋላ ወሰኑ ባሕሩ ላይ ይቆማል። የምድሪቱ ምዕራባዊ ወሰን የታላቁ ባሕር ጠረፍ ነው።
ኢያሱ 15:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው። በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕር ልሳን ነበረ። ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፥ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፥ ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፥ ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በወንዙ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ተመለከተ፥ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፥ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፥ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፥ ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ። ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፥ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ቤትሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ወደ ሽክሮን ደረሰ፥ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
ኢያሱ 15:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የይሁዳ ነገድ ድርሻ በየወገናቸው እስከ ኤዶም ድንበር፥ ወደ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ ይደርሳል። ደቡባዊው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዩ እስከ ሆነው እስከ ልሳነ ምድሩ ነበር። ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከዐቅራቢም መተላለፊያ እስከ ጺን ይደርሳል፤ በቃዴስ በርኔ ደቡብም በኩል ሔጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ከፍ ይልና ወደ ቃርቃ አቅጣጫ ይታጠፋል። ወደ ዓጽሞንም በመዝለቅ፥ በግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘው ወንዝ፥ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይከተላል፤ ያም የድንበሩ መጨረሻ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል የይሁዳ ድንበር ይህ ነው። በምሥራቅ በኩልም ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር፥ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻ ነበር። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር ከዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻና ከባሕሩ ልሳነ ምድር እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል። ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ተነሥቶ ወደ ዳቢር ይወጣል፤ በሰሜን በኩልም አድርጎ ወደ ጌልጌላ ይመለሳል፤ እርሱ ከአዱሚም ትይዩ ይኸውም ከሸለቆው በደቡብ በኩል ነው፤ ስለዚህ ድንበሩ በኤንሼሜሽ ምንጭ በኩል ያልፋል፤ መጨረሻውም ኤን ሮጌል ነው። ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል። ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤ ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል። ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ የምዕራባዊው ዳርቻ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና ጠረፉ ድረስ ነው፤ ይህም የይሁዳ ልጆች እንደየወገናቸው ዙሪያ ድንበራቸው ነው።
ኢያሱ 15:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የይሁዳም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዮ እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ። ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ ዓጽሞንም አለፈ፥ በግብጽም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤ ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፤ ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በሸለቆው በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ታጠፈ፤ ድንበሩም ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ ማብቂውም በዓይንሮጌል አጠገብ ነበረ፤ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤ ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤ ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። በምዕራብም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ። ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።