ኢያሱ 10:24-26
ኢያሱ 10:24-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነዚያንም ነገሥት ወደ ኢያሱ ባመጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎችን አለቆች “ቅረቡ፤ በእነዚህም ነገሥት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ” አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ። ኢያሱም፥ “በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ እግዚአብሔር ያደርጋልና አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ጽኑ፤ አይዞአችሁ” አላቸው። ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፤ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛፎቹ ላይ ተሰቅለው ቈዩ።
ኢያሱ 10:24-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እነዚህን ነገሥታት ባመጡለትም ጊዜ፣ ኢያሱ መላውን የእስራኤልን ወንዶች ከጠራ በኋላ ዐብረውት የመጡትን የጦር አዛዦች፣ “ወደዚህ ቅረቡና እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት ዐንገት ላይ አድርጉ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግራቸውን በነገሥታቱ ዐንገት ላይ አሳረፉ። ኢያሱም፣ “አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በርቱ፤ ጽኑ፤ እንግዲህ በምትወጓቸው ጠላቶች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር እንደዚሁ ያደርጋልና” አላቸው። ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው፤ በዐምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስኪመሽ ድረስ አልወረደም ነበር።
ኢያሱ 10:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የሰልፈኞች አለቆች፦ ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ። ኢያሱም፦ እግዚአብሔር በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፥ ጽኑ፥ አይዞአችሁ አላቸው። ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፥ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፥ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ።
ኢያሱ 10:24-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወደ ኢያሱም አመጡአቸው፤ ኢያሱም የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ጠራ፤ ከእርሱ ጋር የዘመቱት የጦር መኰንኖችም መጥተው እግራቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ። ኢያሱም ለጦር መኰንኖቹ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር ጦርነት በምትገጥሙአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ልክ እንደዚህ ስለሚያደርግ አትፍሩ አይዞአችሁ፤ ቆራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ። ከዚህም በኋላ ኢያሱ አምስቱን ነገሥታት ገድሎ በአምስት ዕንጨት ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስከ ምሽት ድረስ በዚያው ዋለ።
ኢያሱ 10:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎቹን የጦር አዛዦች እንዲህ አላቸው፦ “ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ።” ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፤ ጽኑ፥ አይዞአችሁ።” ከዚህም በኋላ ኢያሱ መትቶ ገደላቸው፥ በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ።