ኢያሱ 10:1-15

ኢያሱ 10:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ ገባ​ዖን ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች እንደ አን​ዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ​ሆ​ነች፥ ከጋ​ይም ስለ በለ​ጠች፥ ሰዎ​ች​ዋም ሁሉ ኀያ​ላን ስለ ነበሩ እጅግ ፈራ። ስለ​ዚ​ህም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ወደ ኬብ​ሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የር​ሙት ንጉ​ሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉ​ሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶ​ላም ንጉ​ሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥ “ወደ እኔ ኑ፤ ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር ሰላም አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ገባ​ዖ​ንን ለመ​ው​ጋት አግ​ዙኝ” አለ። አም​ስ​ቱም የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙት ንጉሥ፥ የላ​ኪስ ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላም ንጉሥ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ጋር ተሰ​ብ​ስ​በው ወጡ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጋር ሊጋ​ጠሙ ከበ​ቡ​አት። የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት። ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑም ሁሉ ከጌ​ል​ጌላ ወጡ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው በፊ​ትህ የሚ​ተ​ርፍ የለም፤” አለው። ኢያ​ሱም ከጌ​ል​ገላ ሌሊ​ቱን ሁሉ ገሥ​ግሦ በድ​ን​ገት ደረ​ሰ​ባ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ታላቅ መም​ታት መታ​ቸው። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ። ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም። ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።

ኢያሱ 10:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን ይዞ እንደ ደመሰሳት፣ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ማድረጉን፣ የገባዖን ሰዎችም ከእስራኤል ጋራ የሰላም ውል አድርገው በአጠገባቸው መኖራቸውን ሰማ። በዚህም እርሱና ሕዝቡ ደነገጡ፤ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ፣ በስፋቷም ከጋይ የምትበልጥ፣ ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ። ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣ “ወደዚህ ወጥታችሁ አግዙኝ፤ ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋራ ሰላምን መሥርታለችና ገባዖንን እንምታ” አላቸው። ከዚያም ዐምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የያርሙት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን አስተባብረው፣ ሰራዊታቸውንም ሁሉ ይዘው በመውጣት ገባዖንን ወጓት። የገባዖንም ሰዎች በጌልገላ ወደ ሰፈረው ወደ ኢያሱ፣ “በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው ተሰልፈውብናል፤ እኛን ባሮችህን አትተወን፤ ርዳን፤ ፈጥነህ በመድረስም አድነን” ሲሉ ላኩበት። ስለዚህ ኢያሱ ምርጥ የሆኑትን ተዋጊዎች ሁሉ ጨምሮ ሰራዊቱን በሙሉ ይዞ ከጌልገላ ወጣ። እግዚአብሔርም ኢያሱን፣ “አትፍራቸው፤ ሁሉንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻቸዋለሁ፤ አንዳቸውም እንኳ ሊቋቋሙህ አይችሉም” አለው። ኢያሱ ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ ዐድሮ ድንገት ወረራቸው። እግዚአብሔርም የአሞራውያንን ነገሥታት በእስራኤል ፊት አሸበራቸው፤ በገባዖን እጅግ መታቸው፤ ወደ ቤትሖሮን በሚያስወጣውም መንገድ ሽቅብ ተከተላቸው፤ እስከ ዓዜቅና እስከ መቄዳም ድረስ አሳድዶ መታቸው። ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ። እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤል አሳልፎ በሰጠባት ዕለት፣ ኢያሱ እግዚአብሔርን በእስራኤል ፊት እንዲህ አለው፤ “ፀሓይ ሆይ፤ በገባዖን ላይ ቁሚ፤ ጨረቃም ሆይ፤ በኤሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በዪ።” ስለዚህ ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ፣ ፀሓይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ፀሓይ በሰማዩ መካከል ቆመች፤ ለመጥለቅም ሙሉ ቀን ፈጀባት። እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ዕለት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አልነበረም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተዋግቶ ነበርና። ከዚያም ኢያሱ ከመላው እስራኤል ጋራ ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።

ኢያሱ 10:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንዲህም ሆነ፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ሆነች፥ ከጋይም ስለ በለጠች፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ። ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፦ ወደ እኔ ውጡ፥ ከኢያሱና ከእስራኤልም ልጆች ጋር ሰላም አድርገዋልና ገባዖንን ለመምታት አግዙኝ አለ። አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት። የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፦ ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፥ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም አሉት። ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ። እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፥ ከእነርሱም አንድ ሰው የሚቋቋምህ የለም አለው። ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው። እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፥ በገባዖንም ታላቅ መምታት መታቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በመንገድ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው። ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ በቤትሖሮን ቁልቁለት ሲወርዱ፥ ወደ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፥ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ። እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ፥ በእስራኤልም ፊት እንዲህ አለ፦ በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፥ ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም። ኢያሱም ከእርሱ ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈራቸው ወደ ጌልገላ ተመለሱ።

ኢያሱ 10:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢያሱ የዐይን ከተማ በጦርነት ከያዘ በኋላ በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ባደረገው ዐይነት በፍጹም የደመሰሳት መሆኑንና ንጉሥዋንም መግደሉን የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሰማ፤ እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር ስምምነት አድርገው በሰላም መኖራቸውን ተረዳ። ገባዖን በነገሥታት እንደሚተዳደሩት ከተሞች ትልቅና ከዐይ ትበልጥ የነበረች ከተማ ከመሆንዋም በላይ ሰዎችዋም ብርቱ ጦረኞች ስለ ነበሩ፥ አዶኒጼዴቅ በጣም ፈራ። ስለዚህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሆሃም ተብሎ ለሚጠራው ለኬብሮን ንጉሥ፥ ፒራም ለተባለው ለያርሙት ንጉሥ፥ ያፊዓ ለተባለው ለላኪሽ ንጉሥና ደቢር ለተባለው ለዔግሎን ንጉሥ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር በሰላም አብሮ የመኖር ስምምነት ስላደረገች እርስዋን ለመውጋት መጥታችሁ እርዱኝ፤” እነዚህ የኢየሩሳሌም፥ የኬብሮን፥ የያርሙት፥ የላኪሽና የዔግሎን ገዢዎች አምስቱ አሞራውያን ነገሥታት ሠራዊታቸውን አስተባብረው፥ የጦር ግንባር በመፍጠር፥ ገባዖንን ከበው አደጋ ጣሉባት። የገባዖን ሰዎችም ሰፈሩን በጌልገላ አድርጎ ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት፦ “በተራራማው አገር የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ እኛን ሊወጉን ስለ ተባበሩብን እኛ አገልጋዮችህን ችላ አትበል! በቶሎ ወደ እኛ ወጥተህ እርዳንና አድነን!” ስለዚህም ኢያሱና መላው ሠራዊት፥ ምርጥ የሆኑት ወታደሮች ጭምር ከጌልጌላ ወጥተው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው። ኢያሱም ሌሊቱን ሙሉ ከጌልጌላ ወደ ገባዖን ሲገሠግሥ ዐድሮ በአሞራውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ ጣለባቸው። እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው። አሞራውያን በመተላለፊያው ቊልቊለት ከእስራኤላውያን ሠራዊት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እስከ ዐዜቃ ድረስ ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ ስለዚህም እስራኤላውያን ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶው ድንጋይ የሞቱት እጅግ ብዙዎች ነበሩ። እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ። ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፤ ጨረቃም ካለችበት ሳትንቀሳቀስ ቈየች፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ሳይንቀሳቀስ በሰማይ መካከል ቆመ፤ ቀኑንም ሙሉ ሳይጠልቅ ቈየ፤ እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር። ከዚህ በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ በጌልገላ ወደ ነበረው ሰፈር ተመለሱ።

ኢያሱ 10:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ነበረች፥ ከጋይም ስለ ምትበልጥ፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ። ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ ዔግሎም ንጉሥም ወደ ዳቤር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወደ እኔ ውጡ፥ ከኢያሱና ከእስራኤልም ልጆች ጋር የሰላም ስምምነት አድርገዋልና ገባዖንን ለመምታት አግዙኝ።” አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የዔግሎም ንጉሥ፥ እነርሱና ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ በገባዖንም ዙርያ ሰፈሩ በእርሷም ላይ ጦርነት አደረጉ። የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።” ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ። ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድም ሰው የሚቋቋምህ የለም።” ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሦ በድንገት መጣባቸው። ጌታም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፤ በገባዖንም በጽኑ ውግያ ድል አደረጓቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በሆነው መንገድ ላይ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው። ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ የቤትሖሮንን ቁልቁለት በመውረድ ላይ ሳሉ፥ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ። ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤” ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመች፥ ጨረቃም ዘገየች። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ጸንታ ቆመች፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለችም። ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም። ኢያሱም ከእርሱ ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈራቸው ወደ ጌልገላ ተመለሱ።